Saturday, November 23, 2013

ፋሽስት ወያኔ በጅዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽ/ቤቱን ላልተወሰነ ጊዜ መዘወጋቱን አስታወቀ

     በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በተለያዩ ቦታዎች የወገኖቻችን ስቃይ ዋይታና ግድያ አሁንም አላቆመም፤ በእያንዳንዷ ደቂቃ ምን ይፈጠር ይሆን በማለት በጭንቅ በጥብ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን ወደ ሀገራቸው የመመለሰቸው ተስፋ አይሎ ባለበት በአሁኑ ሰአት ፋሽስት ወያኔ አገልግሎት እንደማይሰጥ በማስታወቅ የጅዳውን ቆንስላ ጽ/ቤቱን መዝጋቱን በማስታወቂያ መግለጹ ከወደ ሳዉዲ አረቢያ እየተሳማ ነው።
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በወገኖቻቸው ላይ እየደረሰ ያለውን መስመር የሳተ ግፍና በደል ለማስቆም፤ በያሉበት ድምጽ ለሌላቸው ወገኖቻችን ድምጽ በመሆን የሳውዲውን መንግስት በዓለም ዙሪያ በማጋለጥና የዲፕሎማሲ ውጥረት ውስጥ ለመክተት እየጣሩ ባሉበት ባሁኑ ሰአት፤ ፋሽስት ወያኔ የአንበሳውን ድርሻ መጫወት ሲገባው በጅዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽ/ቤቱን መዝጋቱ ብዙዎችን አሳዝኗል። ወደ ሀገራችን እንመለሳለን የሚል እንጥፍጣፊ ተስፋ ሰንቀው እየጠበቁ የነበሩ ተጎጂ ወገኖቻችንንም ተስፋ የሰበረ እንደሆነ ታውቋል።
“በአሁኗ ሰአት ወገኖቻችን በሞትና በሂዎት መካከል ተይዘው በርሃብ በጥምና በብርድ እየተሰቃዩ ይገኛሉ” የሚሉ አንዳንድ ወገኖች “ፋሽስት ወያኔ ለዜጎቹ የሚያስብ ቢሆን ኖሮ ዓለመቀፋዊ እገዛ በመጠየቅ አፋጣኝ ርዳታ መስጠት በተገባው ነበር፤ እያደረገው ያለው ግን የነበረውን እንኳ መዝጋት ነው” ካሉ በሗላ “ስለ እኛ የሚቆምና የሚያግዘን መንግስት የሚባል አካል እንደሌለ ራሳችንን እናሳምንና ባቅማችንና በቻልነው ሁሉ ለወገኖቻችን ራሳችን እንድረስላቸው” ይላሉ።
ከዚህ በፊት በቀደመው የፋሽስት ወያኔ የጫካ ዘመን ወቅት ባስር ሽዎች የሚቆጠር የትግራይ ወገናችን በርሃብ ሲረግፍ፤ ፋሸስት ወያኔ በርሃብ እያለቀ በነበረው ወገናችን ስም ከዓለም ዙሪያ የተቀበለውን የትየለሌ ርዳታ ከችግረኛው አፍ እየነጠቀ ለግል ጥቅም በአውሮፓ በሚገኙ ባንኮች ማስቀመጡን የሚያስታውሱ ሌሎች ወገኖች ደግሞ “ወያኔዎች ከራሳቸው በቀር ሌላ ዘመድ የላቸውም የኢትዮጵያን ሕዝብም ሆነ ባሁኑ ሰአት በሳውዲ አረቢያ ጥቃት እየደረሰበት ያለውን ወገናችንን ጥቅም እስካስገኘላቸው ድረስ ብቻ ነው ወገኔ የሚሉት ካልሆነ ግን ለምንም ደንታ የላቸውም” ይላሉ።
ፋሽስት ወያኔ ለአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭና የግዳጅ መዋጮ ወቅት በሳውዲ አረቢያም ሆነ በአጎራባች ሀገሮች እየተዟዟረ ከነዚህ ዛሬ ችግር ላይ ከሚገኙ ወገኖቻችን በተደጋጋሚ ገንዘብ መሰብሰቡ ሲታወስ፤ እውነትም ፋሽስት ወያኔ ዜጋ የሚለን ገንዘብ እስካለንና እስከደጎምነው ድረስ ብቻ መሆኑን ያረጋግጣል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። ፋሽስት ወያኔ ጥቃት አድራሹን የሳውዲ መንግስት ለማውገዝ ድፍረት ማጣቱ ብቻም ሳይሆን ድርጊቱን ተቃውመው በአዲስ አበባ በሳውዲ ኢንባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ የወጡ ወገኖቻችንን በቆመት እየቀጠቀጡ ማባረራቸውና ጥቂት የማይባሉትንም ማሰራቸው በሳውዲ ለሚገኙ ወገኖቻችን መከራና ግድያ ከሳውዲ መንግስት ገር ተስማምተዋል የሚሉ ወገኖችን አበራክቷል።
 

No comments:

Post a Comment