ከዚህ በፊት በኢትዮጲያ ያለው የሳውዲአረቢያ ኤምባሲ ለአክራሪነት እርዳታዎችን ያደርጋል ለዚህም ደግሞ ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት አላቸው ያለውን በኦሮሚያ ክልል አክራሪነትን አስፋፍተዋል የተባሉት የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሐቢባ መሐመድ የእምነት ነፃነትን በመቃረን ከራሳቸው አክራሪ አስተሳሰብና አስተምህሮት ውጪ በኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ እምነትና ሃይማኖት መኖር የለበትም በሚል ሃይማኖታዊ መንግሥት ለማቋቋም ሲንቀሳቀሱና ሲያስተባብሩ ተይዘዋል እያለ ወያኔ ሲከስ ዛሬ ደግሞ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰያለውን ግፍ እና መከራ ያበቃ ብሎ በኢትዮጲያ ባለው የሳውዲአረቢያ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣውን ህዝብ መደብደብ ማሰር ማገድ ምን ማለት ነው? ስለ ወገኖቹ መቆርቆር ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ምኑ ላይ ነው ክፋቱ? እኔ ያልኩት ብቻ ማለት ካልሆነ በስተቀር ይህ ምን የሚሉት ነው?ለዛውም ለአፍሪቃ ዲሞክራሲን ያሳየን እኛ ነን ለኢትዮጲያ የማውቀው እኔ ነኝ ከሚለው ወያኔ ስራ በዛብኝ የተቃዋሚዎችን ስራ ሁሉ ደርቤ እየሰራሁ ነው የሚል የሃገር መሪ ነኝ ያለን ዛሬ ግን ምን ነካው ተቃዋሚዎች ናቸው ለህዝብ ሲቆረቆሩ ሲጮሁ ሲሰሩ የሚታዩት ለዛውም መሰራት ያለበትን ትንሹን ስራ አትሰሩም እየተባሉ ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ እንዲሉ ሆነ ሁሉም ነገር ግዜ ይወስዳል እንጂ ወደ ፍርድ መመጣቱ አይቀርምና ለዛውም በህዝባቸው ግፍ የሚያደርጉ በአለም አቀፍ ፍርድቤት ቀርበው በሚፈረድባቸው ዘመን ቀኑ አሁንም አልመሸም ከዚህም የከፋ እንዳይመጣ አይምሮአችንን ለበጎ ብንጠቀምበት እና ለኢትዮጲያ ህዝብ ሁሉ የሚበጀውን ብንሰራ ጥሩ ነው
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ
እግዚአብሄር ኢትዮጲያን ይባርክ
ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ
እግዚአብሄር ኢትዮጲያን ይባርክ
No comments:
Post a Comment