የአማራ ክልል መሬቶች ለሱዳን እንዲሰጡ ከገዢው ሕወሓት ጋር በመተባበር ወንጀል፣ እንዲሁም ከጉራፈርዳ ተባረው ወደ አማራ ክልል የመጡ ዜጎች የሚቀበላቸው የክልል መስተዳድር ጠፍቶ ለርሃብና ለሞት በመዳረጋቸው በዚህም ወንጀል እንደሚጠየቁ የሚነገርላቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን አስረከቡ።
መንግስታዊ ሚድያዎች አቶ አያሌው ጎበዜ “በመተካካት” ሂሳብ ስልጣኔን ተረክበውኛል ሲሉ ይዘግቡ እንጂ የአማራ ክልል ምክር ቤት በአስቸኳይ ተሰብስቦ ይሄን ውሳኔ ማጽደቁ ከበስተጀርባው የተደበቀ ምስጢር ሳይኖር እንዳልቀረ ብዙዎች ይገምታሉ። በተለይም አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ሰሞኑን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሱዳን ጋር የኢትዮጵያን መሬቶች አሳልፈው ለመስጠት ከተፈራረሙ በኋላ የአቶ አያሌው ስልጣኔን ልልቀቅ ጥያቄ ምንልባትም ለሱዳን ከሚሰጠው የኢትዮጵያ መሬት ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል አስተያየታቸውን ለዘ-ሐበሻ ሰጥተዋል።
ተሾመዋል። አቶ ገዱ የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንትና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን አቶ አያሌው አልፈጽምም ሲሉ የነበሩ ሥራዎችን ለሕወሓት በማደር ይሰሩ እንደነበር እርሳቸውን የሚያውቁ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ጠቁመዋል። በተለይም አምባገነንና እኔ ያልኩት ይድመጥ የሚል ባህሪይ እንዳላቸው የሚነገርላቸው አቶ ገዱ የአማራ ክልል ስር ያሉ የኢትዮጵያ መሬቶችን ለሱዳን በመስጠት ከሕወሓት ጋር አብረው እንደሚሰሩ ይጠበቃል።
አቤል የተባሉ በክልሉ የሚኖሩ በፌስቡክ ዘ-ሐበሻን የሚከታተሉ አንድ አስተያየት ሰጪ በሰጡት አስተያየት “ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ክቡር አቶ አያሌው ጎበዜ ዛሬ በአቶ ደጉ አንዳርጋቸው የተተኩበት አስቸኳይ ጉባኤ አንደምታው ምን ይሆን? ምን አልባት ከሠሞኑ የሚሠሙ ወሬዎችን እልባት ለመስጠት ይሆን? ያ ማለt ዐድርቃይን ለትግራይ፣ መተማን ለሱዳን፣ ጃዊ አካባቢ ያለ የአማራ ክልል ግዛቶችን ለመስጠት መሠናክሉን ከወዲሁ ለማቅለል ይሆን እንዴ? ያ ምርጫ፣ ዘመን ሣይጠናቀቅ ከስልጣን አቶ አያሌውን ማንሣት ምን ማለት ነው? እርሣቸው ለክልሉ ልዑላዊነት መከበር ጥብቅና የሚቆሙ ታማኝ መሪ ስለነበሩ ገለል ለማድረግ የታለመ ሹም ሽር ነው የሚል ግምት አለኝ” ብለዋል።
ሌላው የዘሐበሻ የፌስቡክ ተከታይም እንዲሁ “የአማራን ክልል መሬት ለሌላ አሳልፌ አልሰጥም በማለታቸው ስልጣናቸውን እንደለቀቁ ነው” የማምነው ሲሉ አስተያታቸውን ሰጥተውናል።
አንድ ቀን በኢትዮጵያ ነፃነት ሲመጣ ምንም እንኳ እርሳቸው አልፈረሙም፤ የፈረሙት አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው የሚባል ወሬ ቢኖርም አቶ አያሌው ጎበዜ ለሱዳን በተሰጠው መሬት፣ በአማራ ክልል ለደረሱ ጭፍጨፋዎች፣ በዜጎች መፈናቀል ዙሪያ ላሳዩት ቸልተኝነት ለፍርድ ይቀርባሉ የሚሉ ወገኖች ብዙ ናቸው።
አቶ አያሌው ጎበዜ
የአማራ ክልል አስቸኳይ ስብሰባውን ከትናንት ምሽት ጀምሮ በባህር ዳር ያካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት ክልሉን ላለፉት 8 ዓመት ተኩል የመሩትን የአቶ አያሌው ጎበዜን ጥያቄ ወዲያውኑ በመቀበል ከስልጣን ያወረዳቸው ሲሆን በምትካቸውም በሕወሓት ተላላኪነታቸው ከአቶ ደመቀ መኮንን አይተናነሱም የሚባሉት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተተክተው ተሾመዋል።
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
አቤል የተባሉ በክልሉ የሚኖሩ በፌስቡክ ዘ-ሐበሻን የሚከታተሉ አንድ አስተያየት ሰጪ በሰጡት አስተያየት “ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ክቡር አቶ አያሌው ጎበዜ ዛሬ በአቶ ደጉ አንዳርጋቸው የተተኩበት አስቸኳይ ጉባኤ አንደምታው ምን ይሆን? ምን አልባት ከሠሞኑ የሚሠሙ ወሬዎችን እልባት ለመስጠት ይሆን? ያ ማለt ዐድርቃይን ለትግራይ፣ መተማን ለሱዳን፣ ጃዊ አካባቢ ያለ የአማራ ክልል ግዛቶችን ለመስጠት መሠናክሉን ከወዲሁ ለማቅለል ይሆን እንዴ? ያ ምርጫ፣ ዘመን ሣይጠናቀቅ ከስልጣን አቶ አያሌውን ማንሣት ምን ማለት ነው? እርሣቸው ለክልሉ ልዑላዊነት መከበር ጥብቅና የሚቆሙ ታማኝ መሪ ስለነበሩ ገለል ለማድረግ የታለመ ሹም ሽር ነው የሚል ግምት አለኝ” ብለዋል።
ሌላው የዘሐበሻ የፌስቡክ ተከታይም እንዲሁ “የአማራን ክልል መሬት ለሌላ አሳልፌ አልሰጥም በማለታቸው ስልጣናቸውን እንደለቀቁ ነው” የማምነው ሲሉ አስተያታቸውን ሰጥተውናል።
No comments:
Post a Comment