Monday, December 23, 2013

ለሳዉዲዎች የተሰጠው መሬት – ግርማ ካሳ


ethiopia_land123213
በሕዝብና በአገር ላይ ጥቃት ሲሰነዘር የአገሪቷ መሪ ህዝቡን የመምራትና የማረጋጋት ሃላፉነት አለባቸው። ሳዉዲዎች በኢትዮጵያዉያን ላይ አሰቃቂ ግፍ በፈጸሙ ጊዜ፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ከመምራት ይልቅ ዝምታን መርጠው፣ አንዴ በካታር፣ ሌላ ጊዜ በፖላንድ ሲሽከረከሩ እንደነበረ ሁላችንም የምናዉቀዉ ነዉ። «ጠ/ሚኒስትሩ የት ነው ያሉት ?» የሚል ጥያቄና ትችት እየጠነከረ በመጣ ጊዜ፣ ከሳምንታት በኋላ ብቅ አሉ። በኢቲቪ ቃለ መጠይቅም አደረጉ።
የአቶ ኃይለማሪያም ቃለ መጠይቅ ግን ብዙ አልተመቸኝም። የወገኖቻችንን ቁስልና ሕመም፣ የኢትዮጵያም ዉርደት የተሰማቸው አይመስልም። በሳዉዲ ያሉ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ከወራት በፊት ሁኔታዎችን ኢሕአዴግ አመቻችቶ፣ የተመለሱት ግን በመቶ የሚቆጠሩ ብቻ እንደሆኑ የገለጹት አቶ ኃይለማሪያም፣ «ስደተኞ በጊዜዉ ቢመለሱ ኖሮ ችግሩ አይወሳሰብም ነበር» ሲሉ፣ ለተፈጠረዉ ችግር በዋናነት የተጎዶ ወገኖቻችን ነዉ ተጠያቂ ያደረጉት። አንዳችም በሳዉዲ የተደረገዉን ግፍ የማዉገዝ ሆነ የመቃወም ነገር አላሰሙም። ዶር ቴዎድሮስ አዳኖም እንዳደረጉት፣ ስደተኞችን ሄዶ መጎብኘቱንማ እርሱት። እንደዉም «ይሄ የተፈጠረው ችግር ከሳዉዲ አረቢያ ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት በምንም ሁኔታ አያደፈርሰውም» ሲሉም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ዶር ቴዎድሮስ ከዚያ በፊት «በሳዉዲ ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ እንወስዳለን» ያሉትን፣ በይፋ ነዉ የቀለበሱት። Read in PDF: ለሳዉዲዎች የተሰጠው መሬት

No comments:

Post a Comment