Tuesday, December 31, 2013

የአንድን ህብረተሰብ ችግር የመረዳትና መፍትሄ የመፈለግ ጉዳይ- ምክንያታዊ፣ ስሜታዊ ወይም ሳይንሳዊ መንገድ!


ከፈቃዱ በቀለ
መግቢያ፣
በመጀመሪያ ደረጃ ውድ አቶ ካሳሁን ነገዎ ታዋቂ ሰዎችን ወይም ምሁሮችን ለቃለ-መጠይቅ እያቀረበ አስተያየታቸውንና አመለካከታቸውን እንድናዳምጥና ትምህርት እንድንቀምስ የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። በዚህም መሰረት በአ.አ በ23.12.2013 ዓ.ም ዶክተር ብርሃኑ ነጋን በቅርቡ ለዕትመትና ለንባብ ባበቃው፣ „ዲሞክራሲና ሁለንታዊ ልማት“ በተባለው መጽሀፉ ዙሪያ ምን ማለቱ እንደሆነ ለቃለ-መጠይቅ ጋብዞት አንዳንዶቻችን ለማዳመጥ ችለናል። የቃለ-መጠይቁን ምልልስ በጥሞና ላዳመጠ የዶክተር ብርሃኑ ነጋ መልስ ግልጽና ብዙም የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም።
…ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ያለውን የተወሳሰበ ችግር ከብቃት ማነስ ጋርም ለማያያዝ ሞክሯል። ይህ ችግር በመንግስትም ሆነ በተቃዋሚዎች መሀከል ሲንፀባርቅ ሲታይ፣ ችግሩ በተለያዩ ኃይሎች ዘንድ የተለያየ ግንዛቤ እንዳለ ይጠቁማል። በተለይም በተቃዋሚው መሀከል ያለውን ችግር ሲያብራራ፣ የተወሰነው ኃይል የአገራችንን ችግር `በጥልቀት` ሲመለከትና `ለመፍታት` ሲጥር፣ ሌላው ደግሞ የራሱን አጀንዳ ይዞ በመምጣትና ስሜታዊ ቅስቀሳ በማድረግ የፓለቲካውን መድረክ እንደሚያደፈርሰውና፣ ይህም ዐይነቱም አካሄድ ለተወሳሰበው የአገራችን ችግር ተደራቢ ችግር እንደፈጠረለት ይጠቁማል። እዚህ ላይ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የብቃትን ማነስ ከዕውቀት ጋር መያያዝ እንደሌለበት ለማብራራት ሞክሯል። በእኔ ግምት ግን ብቃት ማነስ የሚለው አባባል በቀጥታ ከዕውቀትና ከልምድ ማነስ ጋር የሚያያዝ ስለሆነ፣ ብቃት ማነስ በሚለው ፈንታ የንቃተ-ህሊና ማነስ የሚለው ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ላነሳው ጥያቄና የህብረተሰብአችንን ችግር ለመረዳትና መፍትሄም ለመፈለግ የተሻለ አካሄድ ይመስለኛል… [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

No comments:

Post a Comment