በግፍ የታሰሩትን መሪዎቻችንን አስመልክቶ ፍርድ ቤት ለህዳር 23 ሰጥቶት የነበረው ቀጠሮ ለታህሳስ 3 መዛወሩ ይፋና መደበኛ ባልሆነ መንገድ መሰማቱ የመረጃ ክፍተት ፈጥሮ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከኮሚቴዎቻችን ጠበቆች አንዱ አቶ ተማም አባቡልጉ በሚዲያዎች ቀርበው ቀኑ ስለመተላለፉ የደረሳቸው ህጋዊ ይዘቱንና ፎርማሊቲውን ያሟላ መረጃ እንደሌለ መግለጻቸውም የቅርብ ቀናት ትውስታ ነው፡፡
የመረጃ ክፍተቱን ተከትሎ መንግስት ረጅሙ ቀጠሮ ሊደርስ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ይህን የመሰለ የቀጠሮ ለውጥ እንደሚኖር መደበኛ ባልሆነ መንገድ መግለጹ ጥቂት በማይባሉ አካላት ዘንድ ጥርጣሬ ፈጥሮ ነበር፡፡ ‹‹ይህን መሰል ድርጊት ህዝቡን ለማዘናጋት ያለመ ሊሆን ይችላል›› የሚል አስተያየትም ከበርካቶች ተሰንዝሯል፡፡
ዛሬ ህዳር 23 መሪዎቻችን ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ሊደረግ እንደሚችል አንዳንዶች አስተያየታቸውን ሰንዝረው የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ግን ኮሚቴዎቻችን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እስካሁን ድረስ ግን አንዳችም ቀጠሮው መቀየሩንም ሆነ ወደታህሳስ 3 መዛወሩን የሚገልጽ ህጋዊ ፎርማሊቲ ያሟላ መረጃ ያልደረሳቸው መሆኑ መታወቁ የአገሪቱን የፍትህ ስርአት ይበልጥ ለትዝብት የሚዳርግ ነው፡፡ አንድ ታሳሪ ስለፍርድ ሂደቱ የተሟላና ህጋዊ ፎርማሊቲውን የጠበቀ መረጃ የማግኘት መብቱ በህገ መንግስቱ የተረጋገጠ ሆኖ ሳለ በተጨባጭ ግን እውነታው ሌላ መሆኑ የመሪዎቻችን የፍርድ ሂደት በፖለቲካዊ ውሳኔ የሚነዳ መሆኑን የሚያሳብቅ ሆኗል!
መንግስት የህዝብ ወኪሎችን ግልጽነት በጎደለውና ህገወጥ በሆነ የፍርድ ቤት ድራማ ማንገላታቱን ያቁም!!!
የህሊና እስረኛ መሪዎቻችን ማንገላታት ህዝበ ሙስሊሙን ማንገላታት ነው!!!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment