Monday, November 25, 2013

የ ታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች ተቃዉሟቸዉን አሰሙ!!!


ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ወገኖች ዛሬ በተካሄደዉ የ ታላቁ ሩጫ ላይ በሳዑዲ ስለሚሞቱና ስለሚንገላቱ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸዉን ሲያሰሙና በመንግስትም ላይ ወቀሳቸዉን በመፈክር እዲዲሁም በዜማ አሰምተዋል፡፡ መንግሰት በዚህ ሩጫ ላይ ህብረተሰቡ የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ እዳይቀበል በአዘጋጀቹ በኩል ቢያሳስብም(ጥቁር ሪቫን እንዳይደረግ) የሀገር ፍቅር ያቃጠላቸዉና የወገኖቻቸዉ ጥቃት ያተሰማቸዉተሳታፊዎች ከፍተኛ የፖሊስና የደህንነት ቁጥጥር ከቁብ ሳይቆጥሩ “በሳዑዲ ነገር እንነጋገር የሳዑዲን ነገር ” ሲሉ አርፍደዋል፡፡ ገና ከመግቢያዉ ጀምሮ ከፍተኛ ፍተሻ ሲደረግ የነበረ ቢሆንም አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ሪቫኑን ትተዉ በጥቁር ኮፍያና ሱሪዎች ሩጫዉን መካፈል ችለዋል(በተቃዉሞዉ የተሳተፉቱ)፡፡
በሳዑዲ ላይ ተቃዉሟቸዉን ሲያሰሙ በነበረበት ወቅትም ዳር ዳር ላይ ቆመዉ ሁኔታዉን ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎችና በእድሜ የገፉ ሰዎች በእልልታ እና በጭብጨባ ያበረታቱዋቸዉ ነበር፡፡ በዚህ አኳኋን የተካሄደዉ ሩጫ(እርምጃ) ወደ መጠናቀቁ ላይ ግን በደህንነቶች የሚነዳዉ(የሚታዘዘዉ) የፖሊስ ሀይል አንድ ቡድን ላይ በማተኮር ከበባ የሚመስል ነገር በማድረግ እየቆራረጡ ወደ ጃንሜዳ ግቢ እዲገቡ በማድረግ በሩ አካባቢ ላይ ሶስት የሚሆኑ ወጣቶችን(በከፍተኛ ሁኔታ መፈክር ሲያሰሙ የነበሩ) አስረዋል፡፡ በዚህ የተደናገጡት ተሳታፊዎችም ጩኸት በማሰማት ወደ ዉስጥ እየተሯሯጡ በመግባት ሩጫዉም ተቃዉሞዉም ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡

ይሰሙ ከነበሩት መፈክሮች ውስጥ በጥቂቱ፡-
Saudi shame on you, . . .stop Saudi, . . . ተከብረሽ የኖርሽዉ(ያስደፈረሽ ይዉደም) ፣. . . ማልያችን ቢጫ ቢሆንም ዉስጣችን አሯል ፣. . . ዋይ ዋይ ለሳዑዲ . . . ፣ ዝም አላችሁ ምነዉ ዝም አላችሁ . . . አስቻላችሁ ምነዉ አስቻላችሁ . . . (ዝም ብለዉ ለሚያልፉ ተሳታፊዎች ይመስለኛል)፣. . . ሳዑዲ መንግስት በኢትዮጵያዊያን ላይ ያደረገዉን ጭፍጨፋ እንቃወማለን ፣ . . . ሀገር አለን እኛም ሀገር አለን ሀገር አለን እኛም ሀገር አለን፣ . . . #Saudi murderer, . . . መንግስት የሳዑዲን መንግሰት ይጠይቅልን ፣ . . . የሳዑዲ መንግሰት ነፍሰ ገዳይ ነዉ ነዉ ነዉ ፣ . . . ታላቁ ሩጫ ታላቁ ሩጫ የኢትዮጵያዊ ብሶት ማስወጫ(ይህ በዜማ) . . .
ይዘገያል እንጂ አፈናዉ ያበቃል!!!
ዉድድሩ ላይ ከነበረች እህት!

No comments:

Post a Comment