Sunday, September 8, 2013

የአዳማ ሰልፍ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቅቋል!!! የኢቴቪ ድራማ ከሸፈ




በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ በአንድነት የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ መሆኑ ታውቋል። የአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ የማይቀር መሆኑን የተገነዘቡት የክልል መስተዳድሮች ሰልፉ የሚጀመርበትን አካባቢ በፌደራል አድማ በታኝና በፖሊሶች እንዲከበብ አድርገዋል፡፡ አስገራሚው ነገር ግን ወደ ሰልፉ መጀመሪያ ቦታ እየተመመ የሚገኘው ህዝብ በዙሪያው እየተከናወነ ለሚገኘው ነገር ቁብ ሳይሰጥ የተዘጋጁ መፈክሮችን እይሰማ መንገዱን ቀጥሏል፡፡ የፖሊሶችና የአድማ በታኞቹ ከበባ የህዝቡን ስነ ልቦና በፍርሃት ለመሙላት እንደሆነ የተረዱ የአንድነት አመራሮች በቁርጠኝነት ያለ ምንም ስጋት ህዝቡ እንዲቀላቀላቸው በማበረታት ሕዝቡም የፍርሀትን ጠርሙስ ሰበሮ ሰልፉን በቆራጥነት ተቀላቅሏል። ሆኖም በአዳማ በተደረገው ሰልፍ ላይ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ እንቅስቃሴ እንደጀመሩ ፖሊስ ከፊት በማስቆም ‹‹እኔ የደረሰኝ በዋናው መንገድ እንደማትጠቀሙ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ መንገድ ማለፍ አትችሉም›› ይላል፡፡ በዚህ ና በዚያ መንገድ በማለት በዚህ ሰዓት መከልከል እንደማይችሉ በመጥቀስ ሰልፈኞቹ በመንገዱ ተቃውሟቸውን በማሰማት ቀጥለዋል፡፡
ሌላው አስገራሚ ትዕይንት በአዳማ አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ተገን አድርጎ የኦሮሚያ ቴሌቭዥን በአዳማ ሊሰራው የነበረው ድራማ ከወያኔው ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጎን ለጎን የተደናቀፈበት መሆኑ ታውቋል:: በዚሁ ሰልፍ ላይ የአንድነት የምዕራብ ቀጠና ሃላፊ አቶ አስናቀ ሸንገማ በኦሮምኛ ቋንቋና ፣የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስዮም መንገሻ ንግግራቸውን ያሰሙ ሲሆን በመጨረሻም ዶክተር ሃይሉ አርአያ ንግግር አድርገዋል፡፡

No comments:

Post a Comment