Friday, September 20, 2013

ወያኔም በስደት (ጌዲዮን ከኖርዎይ)

ወያኔም በስደት (ጌዲዮን ከኖርዎይ)September 20, 2013
ጌዲዮን (ከኖርዎይ)
መቼም እንደወያኔ አገዛዝ ስደት የሰፈነበት የኢትዮጵያ ታሪክ የለም፥፥ ምሁራን፥ ተማሪ፥ ሰራተኛ፥ የሃይማኖት አባቶች፥ ገበሬው፥ ወጣት ወንድሞችና እህቶች፥ ብቻ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተሰዷል፥ አሁንም በመሰደድላይ ነው፥፥ ብዛት ያላቸው ወንድሞችና እህቶቻችንም ከተሰደዱ በኋላም ወይ መንገድ ላይ ወይ ሰው ሃገር ከገቡ በኌላ ህይወታቸውን ያጣሉ ይሰቃያሉ፥፥
በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከገዛ ሃገራቸው በወያኔ/ህወሃት አፋኝ ስርአት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ፥የዲሞክራሲና የነፃነት እጦት፥ የዘረኝነት መስፋፋት፥ የህግ የበላይነት አለመከበር፥ የኑሮው ከአቅም በላይ መሆንና በሌሎችም በበርካታ ምክንያቶች በግፍ ከገዛ ሃገራቸው ተሰደው ከወጡ በኋላ በሚኖሩበትን ሃገር የመናገር የመፃፍና ሃሳባቸውንበነፃ የመግለፅ መብታቸውን በመጠቀም፥ የወያኔ መንግስትንእኩይ ተግባር ለማጋለጥ ይሞከራል፥፥ ይሁንና ይህ እንቅስቃሴ የወያኔ ማህበርን እንቅልፍ እንደሚነሳ ደሞ አያጠያይቅም፥፥
በዚህም ምክንያት ሃገር ቤት ሃሳባቸውን በድፍረት መግለፅ የቻሉት በሙሉ ማለት ይቻላል አሸባሪ የሚል ቅፅል ስም ተለጥፎባቸው በየእስር ቤቱ በማጎር ሰዎችን ለማፈን ቢሞከርም ኢትዮጵያ ደሞሁል ግዜ ሰው አላትና ተተኪው ብቅ ማለቱ አቀረም፥፥ ወደውጩ ልመለስና የዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ምን ሊያረጉት ይችላሉ አይሉኝም፥
ይኅውልዎት፥ አንድ ነገር ላስታውስዎት፥ በኦክቶበር 09-10, 2011 ዓ/ም አቶ መለስ ዜናዊ ወደ ኦስሎ/ኖርዎይ Energy for all በሚል ስያሜ በተጠራው አለም አቀፍ ስብሰባ ላይ እሳቸውን ጨምሮ የብዙ ሃገራት መሪዎች ተገኝተው ነበር፥፥ እናም ከዛ ሁሉ የአለም መሪውስጥ በአቶ መለስ ዜናዊ ላይ ብቻ ነበር የተቃውሞ ሰልፍ የተነሳው፥፥ እናም በኖርዎይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ተየቌቸው፥ ለምንድነው ይሄ ሁሉ የአለም መንገስት ተቃውሞ ሳይደርስበት በርስዎ ላይ ብቻ ይሄ ሁሉ ውርጅብኝ ብሎ ቢጠይቃቸው፥ እሳቸውም አሉ ተዋቸው ይሄ ሁሉ የምታየው የሚንጫጫው ህዝብ እንደጉም በኖ ይጠፋል ብለውት እርፍ፥፥ የሚገርመው ግን እሳቸው እራሳቸው ይህን ባሉ በአመታቸው ብን ብለው ጠፉ፥፥
ዞሮ ዞሮ በዚህ ተቃውሞ ሰልፈኛ እንቅልፍ ያጡት እሳቸውና ተባባሪዎቻቸው እንደጉም በነው ይጠፋሉብለው በዛቱት መሰረት ስደተኛውን ፀጥ ሊያረገው ይችላል ብለው ባሰቡት መሰረት ከኖርዎይ መንግስት ጋር ስደተኞችን ወዳገራቸው መመለስ የሚያስችል ስምምነት አርገው እንደጉም ለመበታተን ሞከሩ፥፣
እንደኔ አመለካከት ለምሳሌ በኖርዎይ ያለውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማብረድ በተለመደው የማስፈራራት የዛቻ መንፈስ ሳይሆን አይቀርም፥
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን በኖርዎይ ሃገር ባለው የመናገር፥ የመሰብሰብና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በመጠቀም የወያኔን ስራ ባላቸው አቅም ሁሉ በመዋጋት ላይ ይገኛሉ፥፥ በዚህም ምክንያት ወያኔ ደሞ ማን ምን እንደሆነ ምን እንደሚያረግ በመከታተል 24 ሰዓት ስራ ይሰራል፥፥ ይህም ምክንያት ነው ሰዎች ወዳገራቸው ቢመለሱ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው የሚያስብለው፥፥
ለመጋለጣቸው ምክንያት የሚሆነው ደሞ ወያኔ ኢትዮጵያውያን በተሰደዱበት ሃገርም ጭምር ድረስ የተቃዋሚ ሃይሎችን እንቅስቃሴ በመከታተል የተለያዩ መረጃዎችን ለማሰባሰብ የሚገለገልባቸው የራሱ ሰዎችን በተለያዩ መንገዶች በማስገባት ስደተኞችን የመሰለል ስራ ከመስራቱም በላይ ማስፈራራት፥ ዛቻ፥ ብዙ ነገር ይሞከራል፥፥
ለምሳሌ አንድ በቅርብ ቀን ከኖርዌጂያን የስለላ መስሪያ ቤት ማለትም PST /Police security service/ Acting Head of Section for counter-intelligence in the Police Security Service የሆኑት Mr. Ole Børresen በ 01.08.2013 በኖርዎይ ከሚገኝ NRK ከተባለ የሃገሪቱ ዋና የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉትቃለ ምልልስ ላይ በግልፅ ተናግረዋል፥፥
Mr. Ole Børresen እንደሚሉት በኖርዎይ ውስጥ ከ5 እስከ 10 የሚሆኑ ሃገሮች ስደተኞችን በመሰለል ስራ ላይ እንደተሰማሩ መረጃው አላቸው፥፥ እሳቸው እንደሚሉት አገር ቤት በሚገኙ በስደተኛ ቤተሰቦች ላይ የተለያዩ ማስፈራራት፥ እንግልት፥ ድብደባና ዛቻ በአምባገነን መሪዎች የሚደረጉ ዋነኛ መሳሪያዎች ናቸው፥፥
Mr. Ole በመቀጠልም ሲናገሩ PST ላለፉት አመታቶች በነዚህ ስደተኞችን በመሰለል ዙሪያ ብዙ ክሶችና አቤቱታዎች እንደደረሳቸውና በስደተኛ ቤተሰቦች ላይም በደረሱ ችግሮች መረጃ እንዳላቸው ለNRK ገልፀዋል፥፥ አክለውም እነዚህ ሁኔታዎች የሚከሰቱትም ከኖርዎይ ውጭ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ለመግባት አስቸጋሪ እንደሚያረገው ተናግረዋል፥፥
Mr. Ole የትኞቹ የስደተኛ ግሩፖች ናቸው የበለጠ ለዚህ ችግር በኖርዎይ ውስጥ የተጋለጡት ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲያብራሩ፥ ሲመልሱ በዋነኝነት በተቃውሞ እንቅስቃሴ አክቲቭ ሆነው እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ማለትም መንግስታቸውን በተለያየ መንገድ የሚቃወሙትንና በተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሚሳተፉ የበለጠ የተጠቁ ናቸው ብለዋል፥፥
ዋናው ነጥብ እነዚህ አምባገነን መሪዎች ከዚህ ለማግኘት የሚሞክሩት ዋነኛው ውጤት በውጭ ሃገር የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶችን በፀጥታ እንዲቀመጡ በማረግ እንዲሁም በሃገር ቤት በሚገኙ የስደተኛ በተሰቦችም ላይ ጫና ማረግ በተጨማሪ የሚጠቀሙዋቸው ዘዴዎች መካከል ሲሆኑ እነዚህ መንግስታት ስራቸውን ለማስፈፀም ከሚጠቀሙዋቸው ዘዴዎች መካከል፣
• የራሳቸውን የስለላ ሰዎች ወደ ኖርዎይ በመላክ መሰለል
• የራሳቸው ዜጎች ላይ ጫና በማረግ ወደዚህ ስራ ማስገባት
• ስደተኞችን በየካምፑ መመልመል ወይንም የራሳቸውን ሰላዮች ስደተኛ አስመስሎ በመላክ
• የስደተኞችን ኮምፒዩተሮች ሃክ በማረግ መረጃዎችን መሰብሰብ
• በየኢምባሲዎቻቸው ያሉ ሰራተኞችን ለስለላ መጠቀምን ያካትታል፥ በመሆኑም ባለፉት አመታት በዚህ ዙሪያ በዛ ባሉ አቤቱታዎችና ክሶች ላይ እንደመስራታችን መጠን በኖርዎይ ውስጥ ያለማቋረጥ እየተከናወነ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል ብለዋል፥፥
በመጨረሻም ስደተኛን በኖርዎይ ውስጥ የሚሰልሉት ሃገራት እነማናቸው ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሙሉ መረጃ ለመስጠት ፍቃድ ባያሳዩም ግን ኢትዮጵያ፥ ኤሪትሪያና ኢራን በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ግዜ ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ እንደሆኑ ገልፀዋል፥፥
በመቀጠልም እስካሁን ኖርዎይ ውስጥ ሆኖ ሲሰል የተያዘ 1 ሰው ብቻ እንደሆነ ገልፀው የሱዳን ዜግነት ያለው የ 38 አመት ሰው እንደሆነ ገልፀው ስደተኞችን የሚሰልሉ ግለሰቦችን ለማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነ ገልፀው ለዚህ የተጋለጡ ስደተኞችም በሃገራቸው ውስጥ ባለው የህግ ከለላ እምነት ከማጣታቸው የተነሳና መጥፎ ኤክስፒርያንስ የተነሳ እዚህ ሃገር ወደ ፖሊስ በመሄድ ፖሊስን ኢንፎርሜሽን ለመስጠት አይደፍሩም ብለዋል፥፥ ይህንንም በመረዳት PST በተለያዩ አጋጣሚዎች ሰዎች በምን አይነት መንገድ ሰላዮችን ሊያቁ እንደሚችሉና እንዴት ባገራቸው መንግስታት እንደሚሰለሉ ምክር መስጠት እንደጀመሩም ተናግረዋል፥፥ በሌላ በኩልም ቢሮአቸው ግለሰቦችንም በግል በመጥራት አንዳንድ የሚሰሩ ስራዎች በኖርዎይ ውስጥ ህገወጥ እንደሆኑ እንደሚናገሩም አስገንዝበዋል፥፥ ይህም የሚደረግበት ምክንያት አንዳንድ ሰዎች የሚሄዱት አካሄድ የሃገራችንን ህግ ካለመረዳት ነው ከሚል ሃሳብ የመነጨ እንደሆነ ተናግረዋል፥፥
ይህም ማለት ግለሰቦቹ ከሃገራቸው መንግስት እዚህ ያለውን እንቅስቃሴ መረጃ እንዲሰጡ የታዘዙ ቢሆንም ግን ደግሞ ይህን ስራ በኖርዎይ ውስጥ ሆኖ ማከናዎን ስለሚያስከትለው ህግና ቅጣት እንነግራቸዋለን ብለዋል፥፥ ይሁን እንጂ የተጣራ መረጃ በተገኘበት ግዜም ኖርዎይ በቀጥታ ለሚመለከተው ሃገር አቤቱታ ወይንም ማስጠንቀቂያ ትልካለች ብለዋል፥፥
ይሁን እንጂ እነዚህ የምናረጋቸው የምክርና የኢንፎርሜሽን አገልግሎቶች በተወሰነ መልኩ ውጤት ቢያሳዩም PST በግለሰቦች ላይ ለሚደርሰው በሲኪዩሪቲ ጉዳይ ላይ የስደተኞችን መሰለል ጉዳይ በተመለከተ አሳሳቢ እንደሆነ ገልፀዋል፥፥
ስለላው ስደተኞችን በመሰለል ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን ባገር ቤት የሚገኙ የስደተኞች በተሰቦች ላይ እንግልትና ጫና በአምባገነን መንግስታት ይፈፀማል በማለት ተናግረዋል፥፥
ለማንኛውም እንበርታ፥ እንጠንቀቅ፥ ለነፃነታችን ሃገራችንም ላይ ሆነ በተሰደድንበት ሃገር እንታገል፥ የነፃነት ቀን ቅርብ ነው፥፥
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ጌዲዮን

No comments:

Post a Comment