Sunday, September 15, 2013
በመሰየሙ የተሰማቸው ደስታ ገለጹ። – ትርጉም ግርማ ሞገስ
አንዱአለም አራጌና ቤተሰቦቹ
“ዘሐበሻን እና ሌሎች ሚዲያዎችን የመድረስ አቅም ያላቸው እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን አንዷለም አራጌን የአመቱ ሰው አድርገው መምረጣቸውን መስማቴ ታላቅ ደስታ ሰጥቶኛል። አንዷለም ለህዝቡ እና ለአገሩ ብዙ ያበረከተ እና የተጠየቀውን መስዋዕት ሁሉ ካለ ምንም ስስት የከፈለ እና በመክፈል ላይ የሚገኝ ድንቅ ግለሰብ በመሆኑ ለአንዷለም ይኽን እውቅና በመለገሳችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1998 ዓ.ም. ከእስር ቤት ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ ደግሞ መድረክን ወደ ህብረት ከፍ ለማድረግ የፖለቲካ ፕሮግራም እና መተዳደሪያ ደንብ አብረን መቅረጽ ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ አንዷለምን አውቀዋለሁ። ብዙ ፍሪያማ አሳቦችን ለግሷል። መድረክ ወደ ግንባር ደረጃ እንዲደርስ ለማድረግም ካለምንም መታከት ሰርቷል። አንዷለም አንድነት ፓርቲን ወክሎ በመድረክ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ወስጥ በነበረበት ጊዜ ለመድረክ ፕሮጀክት መሳካት ብዙ ከጣሩት የአንድነት ሰዎች ውስጥ አንዱ ነበር። ለወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አክብሮት ነበረው። እጅግ ቀና የሆነ የስራ ግንኙነት ነበራቸው። ያኔ እንደማውቀው እና ዛሬም እንደሚመስለኝ አንዷለም መድረክን በሚመለከት ከአንድነት ከሚሰሙ አሉታዊ ድምጾች ጋር አይስማማም። ቀደም ሲልም በዚህ ጉዳይ ላይ ጽኑ ክርክሮች አድርጓል።
አንዷለም ከመኢአድ እና ያኔ ከአንድነት ተነጥለው ከሄዱት ወገኖች (ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ) ጋር ውህደት እንዲደረግ ይፈልግ ነበር። በዚህ አቅጣጫ አንዷለም የአንድነት ፓርቲን ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አግባብቶ ወይዘሮ ላቀች ደገፉ እና አቶ ተመስጌን ዘውዴ ያሉበትን የድርድር ኮሚቴ ፓርቲው እንዲመሰርት አድርጎ ነበር። ሁለተኛ እስር እስከተበየነበት ጊዜ ድረስ ለዚህ ጉዳይ መሳካት በመስራት ላይ ነበር አንዷለም።
አንዷለም ቁርጠኛ የሰላማዊ ትግል ተዋጊ ነበር። የማህተማ ጋንዲ እና የማርቲን ሉተር ተከታይ። የፖለቲካ እንቅስቃሴዎቹ የሚመሩት በእነዚህ ሁለተ ሰዎች ትምህርቶች ነበር። አንዷለምን ሽብርተኛ ነው ወይንም ከሽብርተኞች ጋር ግንኙነት ነበረው ብለው የሚያስቡ ሰዎች ካሉ አዕምሮዋቸውን የሳቱ እና እራሳቸው ሽብርተኞች ናቸው።
አንዷለም የአንድነት ጸሐፊ እና የአንድነት ህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር በነበረበት ጊዜ ለድርጅቱ ስኬት ለሊት እና ቀን ሰርቷል።
ባለቤቱን እና ሁለት ልጆቹን ይወድ ነበር። ቀኑን እና ምሽቱን ለአንድነት ሲሰራ ውሎ ምሽት ላይ ወደ ቤተሰቡ ነበር የሚሄደው። ወደ መዝናኛ ቦታዎች ከመሄድ ፈንታ።
ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሊቀ መንበር
የግል ህይወቱን በሚመለከት፣ አንዷለም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በንጹሕ ልቦና የሚከተል መንፈሳዊ ሰው ነው። አንዷለም “ ግራ ፊትህን በጥፊ ለመታህ ሰው ቀኝ ፊትህን ስጠው። ሌሎች በአንተ ላይ እንዲፈጽሙብህ ያማትፈልገውን አንተም በሌሎች ላይ አትፈጽም።” የሚሉት የእየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ተከታይ ሰው ነው። ሰው አስቀይሞ ወይንም ተሳድቦ አያውቅም። ሲሰደብም መልሶ አይሳደብም። አይበቀለም አንዷለም። ምክርን እና ማጽናናትን ለሚሹ ሁሉ አንዷለም ጊዜ ነበረው።
አንዷለም አዕምሮ-ክፍት እና ግልጽ ሰው ነው። የማዳመጥ ልዩ ችሎታ አለው።
አንዷለምን “የአመቱ ሰው” ብላችሁ መምረጣችሁ ትክክለኛ ውሳኔ ነው። ይገባዋል። ለሁላችሁም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣
የአንድነት ሊቀመንበር
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment