የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRP)
(ዴሞክራሲያዊ/Democratic)
ነሃሴ ፳፱ ቀን ፪ ሺህ ፭ ዓ. ም
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና የተጫወተና ከክፍፍሉ በኋላም ቢሆን በሁለቱም የኢሕአፓ ክፍሎች የማይናቁ ተግባሮች እየተከናወኑ ያሉበት ሁኔታ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ኢሕአፓ አባላቱ ሁሉቅ ወመሳፍርት የሌለው መስዋዕትነት የከፈሉበት ድርጅት ቢሆንም በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠሩ ችግሮችና ከተለያዩ ጠላቶችና ተቀናቃኝ ኃይሎች በደረሱበት ጉዳቶች ምክንያት ከአባላቱ፤ ከደጋፊዎቹና ከሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠበቅበትን ውጤት ሊያበረክት ግን አልቻለም። ይሁን እንጂ በኢሕአፓ (ዴሞክራሲያዊ) ውስጥ የተሰባሰቡት አባላት ትግሉ የሚጠይቀውን ተገቢ እርምጃዎች በመውሰድ ሀገራዊ ትግሉን የበለጠ ለማጠናከር፤ በተለይም በውስጡ ዴሞክራሲያዊ ባህሎችን ለማጎልበት፤ ይህንንም ሊደግፉና ህያው አድርገው ሊያቆዩ የሚችሉ ተቋሞችን በመፍጠር ዓይነተኛ አስተዋጽዖ ማድረግ ይቻላል ከሚል ዕምነት በመነሳት እንዲሁም የኢሕአፓንና የዚያን ጀግና ትውልድ ታሪክ ሳይዛባ በተገቢው መንገድም ለተኪው ትውልድ ማስተላለፍ እንዲቻል በማሰብ የድርሻቸውን እያበረከቱ ይገኛሉ።
ኢሕአፓ (ዴሞክራሲያዊ) ለመለያየት ምክንያት የሆኑትን ችግሮች አርሞና ጎጂ ልማዶችንም አስወግዶ ኢሕአፓን እንደገና የማዋሃዱን ተግባር እንደ አንዱ ዓላማውና ሃላፊነቱም በመውሰድ በጉባኤ ወስኖ፤ ሃላፊነቱን የሚሸከም አካልም አቋቁሞ ላለፉት ስድስት ዓመታት እየሠራበት የነበረ ጉዳይ ነው። በዚህም መሠረት ድርጅቱን አንድ በማድረግ ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ውይይት እንዲጀመር ለተለየናቸው የኢሕአፓ አባላት የጥሪ ደብዳቤ ልኮ ነበር። የጥሪ ደብዳቤውን መሠረት ያደረገ ግልጽ መልስ ባይገኝም በዚህ ረገድ ያለውን ፅኑ አቋምና ዝግጁነት በስብሰባዎችና በመድርኮች በግልጽ ማቅረቡ ይታወቃል።
ኢሕአፓ (ዴሞክራሲያዊ) ድርጅቱ ከተከፋፈለበት ወቅት አንስቶ የተለያዩ የድርጅቱ ወዳጆች ያቀረቡለትን የአስታራቂ ሃሳቦችን ተገቢ ክብደት በመስጠት ለኢሕአፓ አንድነትና ጥንካሬ ያለውን ጽኑ ፍላጎት ያለመወላወል ገልጿል። ውስጣዊ ዴሞክራሲ ለማስፈንና ሀገራዊ ትግሉንም ለማጎልበት አስፈላጊ ሆነው ያገኛቸውን ገንቢ የሆኑ ማሻሻያዎችን ሁሉ እንደሚቀበላቸው ሳይታክት ሲገልጽ ቆይቷል። ኢሕአፓን ለማዋሃድ አባላቱን መድቦ እየሠራ ባለበት ወቅት ነው ተለይተናቸው ከነበሩት አባላት ኢሕአፓን አንድ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ይፋ የተደረገው። ኢሕአፓ (ዴሞክራሲያዊ) ዜናውን የተቀበለው በደስታ ከመሆኑም በላይ ተለይተናቸው ከነበሩት አባላት የመጣውን የአንድነት ሃሳብ በተመለከተ በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ ከሚመለከታቸው አባላት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑንም ይገልጻል።
በሌላው የኢሕአፓ ክፍል ውስጥ ያሉት አባላት “የኢሕአፓ የርማት እንቅስቃሴ … ” በሚል ተሰባስበው የጀመሩት ተግባር ቀላል እንዳልሆነ ነገር ግን አስፈላጊና ወቅታዊ በመሆኑ ኢሕአፓ (ዴሞክራሲያዊ) ጥረታቸውን ከማድነቅ አልፎ በሙሉ ልብ ይደግፈዋል። የተሰባሰበና የተጠናከረ ኢሕአፓ ዛሬ ባለው ውስብስብ የሀገራችን ሁኔታ እንደገና ታሪክ ሊሠራና ለአገርና ለትውልድ የሚበጅ ለውጥ ለማምጣት በሚደረገውም ትግል ላይ ጉልህ ሚና ሊጫወት የሚችል በመሆኑ የኢሕአፓ አንድነት ሊኖረው የሚችለው ታሪካዊ ጠቀሜታ ለአንዳፍታም እንዳይዘነጋ አደራ እንላለን።
አንድነት ኃይል ነው!

No comments:
Post a Comment