1. መግቢያ:
ካለፈው ሁለት አመት ግድም ጀምሮ “መንግሥት በዲናችን ጣልቃ አይግባብን” በሚል ሰፊ ማእቀፍ ውስጥ በሰላማዊ መንገዶ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እየተደረገ ያለው ትግሌ፤ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ደግሞ ሁለት አስርት አመታትን ያስቆጠረ ከቀኖናው ውጭ መንግሥት የቤተክርስቲያኑን መሪ አይምረጥብን በሚል በመሰረታዊ ሀሳቡ ከሙስሉሙ ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጉዳይ በተነሳ ውዝግብ ቤተክርስቲያኒቱ ለሁለት ተከፍላ ያለችበት ሁኔታና በዚህም ምክንያት በመንግሥት የተገፋው “ስደተኛው ሲኖዶስ” በራሱ ላይ የደረሰውን ሁከት በመቃወም የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ተዳምረው ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ ጤነኛ የሆነው የሀይማኖትና የፖለቲካ ግንኙነት ምንዶን ነው? ወይንም ደግሞ የመንግሥትና የሀይማኖት ግንኙነት ምን መሆን አለበት? የሚለውን ጥያቄ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የሀይማኖቱ ተከታዮች አልፎ ያጠቃላይ የፖለቲካ ማህበረሰቡ (የሀገሩ) ትልቅ የመወያያ አርዕስት እየሆነ ነው:: ይህ ጉዳይ ግን ጥቅል ከሆነ ያመለካከትና የንድፈ ሀሳብ ጥያቄ በተጨማሪ ጥልቅና አስቸኳይ የሆነ የተግባር ፖለቲካ ጥያቄም ነው ይዞ የመጣው::
ምንም እንኳን ከቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ አገዛዝ ጀምሮ “ሀይማኖት የግል ነው: ሀገር የጋራ ነው” በሚል አጠቃላይ መፈክር ስር ሀይማኖትና መንግሥት መገናኘት የለባቸውም የሚል አመለካከት በሁለም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ቢመስልም፤ በተግባር ግን ይህ ግንኙነት በተለያዩ ምክንያቶችና መንገዶች በቅርብ ዘመን በነበሩት ሁለም አይነት አገዛዞች እየተጣሰ አመለካከቱን ከመፈክር ያለፈ ተጨባጭ ትርጉም የለለው አድርገውታል:: ያገዛዝ ስርዓቶች ካፈጣጠራቸው ዋና ትኩረታቸው በስልጣን መቆየት ስለሆነ ይህን አላማቸውን ለማሳካት እናምንባቸዋለን የሚሎቸውን መርሆችም እንኳን ለመደፍጠጥ ወደኋላ እንደማይሉ ይታወቃል:: በዚህም ምክንያት አሁን ካለው ሥርዓት በፊት የነበሩትም ያገዛዝ ስርዓቶች ለስልጣናችን ይጠቅመናል ባሉ ጊዜ ሀይማኖትን ለመጠቀም፤ በሀይማኖቶች አሰራር ላይ ጣልቃ መግባት፤ እንደሁኔታው በሀይማኖቶች መሀል ማበላለጥ…ወዘተ የመሰለ ጣልቃ ገብነቶች ተጠቅመዋል:: በዚህም ምክንያት በተለያዩ ጊዜዎች በሀይማኖት ተቋማትና በመንግሥት ወይንም በተለያየ ሀይማኖት ተከታዮች መሀከል የተለያዩ ደረጃዎች ያሎቸው ውጥረቶች ተከስተዋል:: ያም ሆኖ ግን በዚህ በወያኔ ስርዓት የደረሰውን ያክል ፍጥጫና ውጥረት እኔ እስከማውቀው ዶረስ በቅርብ ጊዜ ታሪካችን ደርሶ አያውቅም:: በዚህም ምክንያት ይመስለኛል ይህ ጉዲይ የፖለቲካችን አብይ ጉዳይ መሆኑ:: ……(ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ ከዚህ ላይ ይጫኑ – PDF)
No comments:
Post a Comment