Sunday, June 9, 2013

የግብፅን የአስዋን-አባይ ግድብ ምን ያህል እናውቀዋለን?

    
Aswan high dam
የአስዋን ግድብ
(በዮሴፍ ደግፌ)
የተወደዳችሁ አንባቢያን እንዴት ከረማችሁ? ስለ አባይ ጉዳይ እያሰባችሁበት ነው? ማሰብ ባቻ ሳይሆን ውሳኔም ላይ መደረስ መቻላችን የወቅቱ የዜግነት ግዴታችን መሆኑን አንዘንጋ። ይህች ትንሽ መጣጥፍ፤ በፖለቲካም ይሁን በፕሮፌሽናል ጠጣር ቃላት (Jargon words) ሳትጨናነቅ፤ ለሁሉም አይነት አንባቢ ቀለል ባለ አቀራረብ፤ አባይን “ለሀገሩ-ባእድ-ጠላት፤ ለውጭ-ሲሳይ-በረከት” በማለት ብትወቅሰው ምክንያቴን የማትረዱ አይመስለኝም። ነገርግን ርእሴ “የግብፅን የአስዋን-አባይ ግድብ ምን ያህል እናውቀዋለን?” የሚል ቢሆንም፤ “የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል” ነውና፤ ዞሬ ዞሬ ወደ እኛው ጉዳይ መግባቴና በዚያም ላይ ማተኮሬ አይቀርም። በአለም ላይ በርዝመቱ አንደኛ የሆነውን ታላቁን የአባይን ወንዝ ብቸኛ ምንጩ አድርጎ የተገነባውና፤ የግብፅ ዋነኛ የኢኮኖሚ ዋልታና ምሰሶ የሆነውን የአስዋንን ግድብ አቅም በተመለከተ፤ በራሳቸው በግብፆች እጅ የተከተበውን አጭር የእንግሊዘኛ ፅሁፍ፤ ከዌብ ሳያታቸው ላይ ያገኘሁትን፤ ለግንዛቤ እንዲረዳ፤ ከዚህ ፅሁፍ ጋር አያይዤ አቅርቤዋለሁ። በአባይ ጉዳይ ላይ ሱዳንን ለጊዜውም ቢሆን ትተን፤ የግብፅ የአስዋን ግድብን አቅም (የናይል ግድብ ብለው አለመሰየማቸው መልካም ይሆንን?) ባጭሩ በማቅረብ፤ ወቅታዊውን የአባይ ሁኔታ በጥቂቱም ቢሆን ለመረዳት እንዲያግዝ፤ አባይ ለግብፅ የፈጠራቸውን ጥቅሞች ባጭርና በቀላል አገላለፅ ቀርቦአል። የአስዋን ግድብ ከተገደበና ለግብፅ ጥቅም መስጠት ከጀመረ ከ45 አመታት በላይ (ግማሽ ምዕተ አመት ያህል) እንደሞላውስ ታውቁ ይሆን? አዎን በርግጥ የግብፁ አባይ ‘የአስዋን ግድብ’ ዘመናትን ሲያስቆጥር፤ ኢትዮጵያ በተባለችው ምድር ላይ የሚኖረው የአባይ ምንጭ የሆነው “ምስኪን” ህዝብ ግን፤ በክርስትና ለሁለት ሺ አመታትን ቢቆይም፤ መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚገልፀውም “እንደ እባብ ብልህ፤ እንደ እርግብም የዋህ” አይነት ጥበበኛና አስተዋይ ህዝብ ሆኖ የተገኘ አይመስለኝም። በዚህም ፈጣሪ የሰጠንን በረከትም፤ በራሳችን ምክንያት ለመጠቀም ባለመቻላችን፤ እስከዛሬ ድረስ በአለም ላይ ርሀብተኛ፤ ተመፅዋች፤ ስደተኛና የድህነት ማስረጃዎች ሆነን እንገኛለን። ይኸውም በዘመናት የአዙሪት ጦርነት እስከ ዛሬ ድረስ እርስ በርስ ስንተላለቅ፤ “ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” እንደምንለው ሀገራዊ አባባል ሆነና፤ አባይ፤ አባይ፤ እያልን በዘፈን ብቻ ወንዙን ስናሞካክሽና፤ ምንም ሳይኖረን በባዶ ሜዳ ላይም ለዘመናት ስናቅራራ፤ ታላቁ የሀብት ምንጫችን አባይ፤ ለሀገሩ ባዳና ጠላት፤ ለውጭ ግን ሲሳይና በረከት ሆኖ እስከዛሬ ዘመን ድረስ ዘልቋል። በመሆኑም በግብፅ የአስዋን (አባይ) ግድብ መመዘኛ ብቻ ተሰልቶ፤ ከግብፅ ጋር ብትወዳደር፤ ቢያንስ 50 (ሀምሳ) አመታት ያህል ኢትዮጵያ በልማት ወደሁዋላ ቀርታለች ቢባል ይጋነን ይሆን?
ከ45 አመታት በፊት፤ $1 (አንድ) ቢሊዮን ዶላር የፈጀ ነው። የአስዋን ግድብ 111 (መቶ አስራ አንድ) ሜትር ጥልቀት፤ 4 (አራት) ኪሎ ሜትር የወርድ ስፋትና፤ 22 (ሃያ ሁለት) ኪሎ ሜትር ያህል ርዝመት ያለው፤ ታላቅ የውሀ ሀብት የፈጠረላቸውም መሆኑን ግብፆች በኩራት ይገልፃሉ። በቀድሞው የግብፅ ፕሬዜዳንት ጋማል አብዱልናስር ስም የተሰየመውና
“ናስር” የሚባል የአሳ ሀብት ማርቢያና መሰብሰቢያ፤ እና እንዲሁም ለትራንስፖርትና ለመዝናኛ የሚያገለግል ትልቅ ሰው ሰራሽ ሃይቅ፤ የአባይ ወንዝ ለግብፅ እንደሰራላትና ጠቀሜታውም የትየለሌ እንደሆነ ግብፆች አልሸሸጉም። ኢትዮጵያዊው አባይ ለግብፅ በሀይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫነት ከሚሰጠው ጥቅም በተጨማሪም፤ በየአመቱ 40 (አርባ) ሚሊዮን ቶን ደለል ለም አፈር ከኢትዮጵያ አግበስብሶ ለግብፅ በማበርከቱ፤ ኢትዮጵያን የለም አፈር ደሀ፤ ግብፅን ደግሞ በዘመናዊ ግብርና የለም አፈር ሀብታም ሆና እንድትበለፅግ አባይ በማድረጉ፤ ግኡዝ የሆነውን ውሀ እንደ ባእድ ጠላት መቁጠሬም ለዚህ ነው። ስለዚህም አባይ ለግብፅ በሰባት መንገዶች የኢኮኖሚ ጥቅም (መሰረት) ሆኖ ማገልገሉን ብንረዳ፤ እኛስ? የሚል በጎና ተገቢ ቁጭት፤ ለስራም የሚያነሳሳ እልህ ለማሳደር ይጠቅመናል። 1ኛ/ በሀይድሮ (የውሀ ሃይል) ኤሌክትሪክ ምንጭነት፤ 2ኛ/ የአሳ ሀብት ማርቢያና መሰብሰቢያ ሀይቅነት፤ 3ኛ/ በውሀ ትራንስፖርትነትና የመዝናኛ አገልግሎት ሰጭነት፤ 4ኛ/ በመስኖ ግብርና ልማት፤ 5ኛ/ የድንግልና ለም አፈር ግብርና በረከት (Organic Soil Agriculture) 6ኛ/ በምግብና በመጠጥ ውሀ ተቀሜታነትና 7ኛ/ በረሀማነትን የመቀነስ ጥቅም ዋነኞቹ ናቸው።
መልካም ነው፤ እንኳንም አባይ ግብፅን ጠቀመ፤ አበለጠገም፤ ኢትዮጵያም በግብፅ ልማትና ብልጥግና ቀንታ፤ ግብፅን በጦርነት ወርራ የግብፅን ልማት ላውድም፤ አባይንም ለብቻዬ ልጠቀም አላለለችም። ኢትዮጵያ ያለችው ነገር ቢኖር፤ ባጭር ምሳሌ የሚከተለውን ነው። “አንድ ቤተሰብ በቤቱ ውስጥ ያዘጋጀውን ምግብ ለመብላት፤ ጎረቤቱን ሄዶ ማስፈቀድ አያስፈልገውም ” ነው። ማለትም፤ ኢትዮጵያ አባይን በመገደብ የዘመናት ድሀ ህዝብዋን ለመጥቀም፤ ግብፅን ማስፈቀድ አይገባትም ነው፤ ባጭር አነጋገር። ታዲያ! ለአባይ ምንጭ/መነሻ ያልሆነችው ግብፅ እንኳን ይህንን ያህል በአባይ የውሀ ሀብት መጠቀም ከቻለች፤ የአባይ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ ብዙ ዘግይታም ቢሆን፤ የውሀ ሀብትዋን ዛሬ ልትጠቀምበት ስትሞክር፤ ግብፅ “እንዴት ተደርጎ?” ለማለት ቻለች? እኔን የሚገርመኝና የሚያሳዝነኝ የግብፅ ማንኛውም አባበል ሳይሆን፤ ነገርግን ኢትዮጵያ የውሀ ሀብትዋን ለመጠቀም ከግብፅ አንፃር 50 (አምሳ) አመታትን ወደ ሁዋላ መቅረትዋ ነው። ይኸውም ኢትዮጵያ፤ ምን ያህል ርሀብን እንደ ብልፅግና ቆጥራ፤ ዜጎችዋን በመከራና በእርዛት ለዘመናት የፈጀች “ከንቱ” አገር፤ ለግብፅ ግን የምትመች ሲሳይ በረከት ለመሆን ቻለች? እያልኩ እያፈርኩም ቢሆን በድፍረት ለመናገር አፈልጋለሁ። ለመሆኑ ኢትዮጵያ አባይን ብትገነባና እንደተባለውም 6000 ያህል( ስድስት ሺ) ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ብታመነጭ፤ ግብፅ የውሃ እጥረት እንደማያጋጥማት የታወቀና፤ የአለም አቀፍ የኤክፐርቶችም ቡድንም ያረጋገጠው ሆኖ ሳለ፤ አሁን ያለው የህ ሁሉ ጫጫታ ከየት የመጣ ይሆን? ግብፅን ይህን ያህል ያሰጋት ከቶ ምንድን ይሆን?
እንደኔ መረዳት ከሆነ፤ ኢትዮጵያ በምትገነባው የአባይ ግድብ ግንባታ ምክንያት፤ ግብፅ ላይ ሊፈጠርባት የማይችለው ምንም አይነት ችግር አይደለም ግብፅን ያሰጋት። ይልቁንም፤ ኢትዮጵያ ከግንባታው በሁዋላ ሊኖራት የሚችለውን ታላቅ የኢኮኖሚ አቅም ግብፅን በርቀት ያስፈራት ይመስለኛል። ይኸውም ከአባይ ግድብ ግንባታ በሁዋላ ኢትዮጵያ ልታመጣ በምትችለው ሁለንተናዊ እድገት የተነሳ፤ በአፍሪካ አህጉርም ይሁን በአለም አቀፍ ደረጃ፤ ሀገራችን ልትፈጥር በምትችለው ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ (ምናልባትም ወታደራዊ) እና ዲፖሎማሲያዊ ተፅእኖዎች ቅድመ ምክንያቶች፤ ግብፅ አስቀድማ ሰግታ እንደሆነ ነው’ንጂ፤ (ይህም የሚያሰጋ አልነበረም “አያ ጅቦ ሳታማኻኝ ብላኝ” ይመስላል) ኢትዮጵያ አባይን በመገደብዋ ምክንያት፤ የግብፅ አለምአቀፋዊ መብትም ሆነ፤ አሁን ያላት የውሀ ጥቅም የሚነካባት ሆኖ አይደለም። እንዲያውም በተቃራኒው ግብፅንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራ ነው ኢትዮጵያ የምትሰራው። ዝርዝሩን ለውሀው ለባለሙያዎቹ እተወዋለሁ። ስለሆነም ኢትዮጵያ-ሀገሬ-ሀገሬ የሚል ሁሉ፤ ይህንን ማስተዋልና መረዳት ካልቻለና፤ በጋራ ለመስራትም ካልተነሳ፤ በግሎባላይዜሽን ዘመንም ላይ ሆነን፤ እንደሰው እያሰብን፤ እንደሰው የምንኖር ሰዎች መሆናችንን፤ አለም ሁሉ የሚጠራጠረን ብቻ ሳይሆን፤ መሳቂያና መሳለቂያም የሚያደርገን መሆኑን አንርሳ እላለሁ። “ከእኔ በላይ አዋቂ’ ለሀገርም አሳቢ ላሳር” ወይም “ከእኛ ወዲያ ፉጨት አፍ ማሞጥሞጥ” ከሚባለው፤ ሀገርኛ ጎጂ አባባል ነፃ እንውጣና፤ የመደራደርና የመቻቻልን ጥበብና እውቀትን አዳብረን እንነጋገር፤ ተነስተንም አብረን እንስራ።
ስለዚህም፤ ለእኛ፤ ለዛች ለመከረኛ ምድር ሰዎች፤ የሚከተለውን አጭር መልእክት በጥቅሉ አስተላልፌ፤ ፅሁፌን ለግዜው በዚህ ላይ ላብቃ። ከአባይ ግድብ ግንባታ በፊት “ሰብአዊ መብት፤ ዲሞክራሲና የህግ የበላይነት (ፍትህ) ይገንባ !!!” የምንልም እንሁን፤ “ታላቁን ጠላት ድህነትን አስቀድመን እንዋጋ !!!” የምንል ሁላችን፤ የአባይ ግድብ ግንባታን ጉዳይ ያንድ ወገን/ግሩፕ/ፓርቲ ጉዳይ ሳይሆን፤ የሁላችንም ጉዳይ ነውና፤ በአባይ ጉዳይ ማንም ማንንም እንዳናገልል ሁላችንም እንጠንቀቅ፤ አጥርተንም እንመልከት፤ አርቀንም ለትውልድ እናስብ ዘንድ ይገባል። ስለሆነም፤ እርስ በርስ ጥላቻን በማስወገድ፤ በምትኩም ፍቅርንና መተሳሰብን በመተካት፤ በአባይ ግንባታ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ታላላቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ፤ ብሄራዊ መግባባትን በመፍጠር፤ ባንድነት ተስማምተን የሚገባንን እንድናደርግ፤ የልብ አይኖቻችንን እግዚአብሄር ያብራልን የሚል ፀሎት ብቻ፤ የእኛ ፈቃደኝነት ከሌለበት ከምኞታችን ያለፈ ዋጋ የሌለው መሆኑን እንዳንረሳ ያስፈልጋል። ህብረትና አንድነት፤ ሰላምና ልማት፤ ለምድራችን የሚመጣው በእኛ በሁላችን ፈቃድ ብቻ ሲሆን ነውና፤ አሜን ይሁንልን!!! የአስዋን ግድባቸውን የተመለከተው የግብፆች ፅሁፍ በአረብኛ ሳይሆን በእንግሊዝኛ ከዚህ በታች እንደሚከተለው የከተቡትን እነሆኝ።
Aswan High Dam, Arabic Al-Sadd al-ʿĀlī, rockfill dam across the Nile River, at Aswān, Egypt, completed in 1970 (and formally inaugurated in January 1971) at a cost of about $1 billion. The dam, 364 feet (111 metres) high, with a crest length of 12,562 feet (3,830 meters) and a volume of 57,940,000 cubic yards (44,300,000 cubic metres), impounds a reservoir, Lake Nasser, that has a gross capacity of 5.97 trillion cubic feet (169 billion cubic metres). Of the Nile’s total annual discharge, some 2.6 trillion cubic feet (74 billion cubic metres) of water have been allocated by treaty between Egypt and Sudan, with about 1.96 trillion cubic feet (55.5 billion cubic metres) apportioned to Egypt and the remainder to Sudan. Lake Nasser backs up the Nile about 200 miles (320 km) in Egypt and almost 100 miles (160 km) farther upstream (south) in Sudan; creation of the reservoir necessitated the costly relocation of the ancient Egyptian temple complex of Abu Simbel, which would otherwise have been submerged. Ninety thousand Egyptian fellahin (peasants) and Sudanese Nubian nomads had to be relocated. Fifty thousand Egyptians were transported to the Kawm Umbū valley, 30 miles (50 km) north of Aswān, to form a new agricultural zone called Nubaria, and most of the Sudanese were resettled around Khashm al-Qirbah, Sudan. The Aswan High Dam yields enormous benefits to the economy of Egypt. For the first time in history, the annual Nile flood can be controlled by man. The dam impounds the floodwaters, releasing them when needed to maximize their utility on irrigated land, to water hundreds of thousands of new acres, to improve navigation both above and below Aswān, and to generate enormous amounts of electric power (the dam’s 12 turbines can generate 10 billion kilowatt-hours annually). The reservoir, which has a depth of 300 feet (90 metres) and averages 14 miles (22 km) in width, supports a fishing industry. The Aswan High Dam has produced several negative side effects, however, chief of which is a gradual decrease in the fertility and hence the productivity of Egypt’s riverside agricultural lands. This is because of the dam’s complete control of the Nile’s annual flooding. Much of the flood and its load of rich fertilizing silt is now impounded in reservoirs and canals; the silt is thus no longer deposited by the Nile’s rising waters on farmlands. Egypt’s annual application of about 1 million tons of artificial fertilizers is an inadequate substitute for the 40 million tons of silt formerly deposited annually by the Nile flood. Completed in 1902, with its crest raised in 1912 and 1933, an earlier dam 4 miles (6 km) downstream from the Aswan High Dam holds back about 174.2 billion cubic feet (4.9 billion cubic metres) of water from the tail of the Nile flood in the late autumn. Once one of the largest dams in the world, it is 7,027 feet (2,142 metres) long and is pierced by 180 sluices that formerly passed the whole Nile flood, with its heavy load of silt.

No comments:

Post a Comment