Saturday, May 4, 2013

ይህ ሰው የወያኔ ሰላይ ነው፣ መልኩን በደንብ ያጥኑት፣ ራስዎን ይከላከሉ

 

ECADF – የዚህን ሰው ፊት በደንብ ይመልከቱ። ይህ ሰው በቅርቡ በወያኔ ተላላኪዎች አማካኝነት አንድ ጽሁፍ ጻፈ ተብሎ ያስነበበን ሰው ነው። ይህ ግለሰብ ባስነበበን ጽሁፍ “በቅርቡ ከግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል እጅግ ፈታኝ ሁኔታዎችን አምልጬ ሱዳን ገባሁ። ሱዳንም ውስጥ ሆኜ ጽሁፍ አውጥቼ ላክሁ። ወደፊትም በቀጣይነት በሌሎች ሚድያዎች ስለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ገለጻ አደርጋለሁ” ብሎናል።EPRDF/TPLF spy in Addis Ababa
ግለሰቡ ቀደም ሲል ይኖር በነበረበት ደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያንና ሌሎችም ግለሰቡን በቅርብ ከሚያውቁት ሰዎች ጋር ተነጋግረን እንዳጣራነው ከሆነ ይህ ሰው በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለምንም ችግር በመንቀሳቀስ ላይ ያለ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። በተጨማሪም፣
1ኛ – ከግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልና ከኤርትራ መንግስት አምልጦ የሄደ ሳይሆን ቀድሞውኑ ለስራ የተመደበው በሱዳን እና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ እንደነበር ለመውጣትም ለመግባትም ምንም ችግር ያልነበረበት እንደነበር፣
2ኛ – ከህዝባዊ ሃይሉ ከድቶ በ24 ሰአት ውስጥ አዲስአበባ ከተማ የደረሰ መሆኑ፣
3ኛ – በወያኔ የደህንነት መስሪያ ቤት ሙሉ ወጭው ተሸፍኖለት በሆቴል ተቀምጦ እንደነበር፣
4ኛ- ይህ ሰው ጻፍኩ በማላት የወጣው ጽሁፍ እሱ በተባባሪነት እንጂ ዋናው ጸሃፊዎቹ የወያኔ የደህንነት ሰዎች መሆናቸውን,፣
5ኛ – ጽሁፉ ወደተለያዩ ሚዲያዎች የተላከው በወያኔ የደህንነት ቢሮ በኩል እንደሆነ፣
6ኛ – ይህ ግለሰብ ሚያዝያ 22፣ 2005 ዓ.ም የወያኔ ደህንነት በቅርቡ ግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይልን በተመለከተ ለማዘጋጀት ላሰበው አኬልዳማንና ጂሀዳዊ ሀረካትን መሰል ድራማ ዋናው ተዋናይ እንዲሆን ኮተቤ ከሚገኘው የቤተሰቦቹ ቤት ፕሮግራሙ ወደሚሰራበት መስሪያ ቤት ተወስዶ ስራ የጀመረ መሆኑን ለማጣራት ችለናል።
ከላይ ያስቀመጥናቸውን መረጃዎች ይዘን ወደ “ግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል” ቃል-አቀባይ ደውለን ነበር። የህዝባዊ ሀይሉ ቃል-አቀባይም ግለሰቡን እንደሚያውቁትና ለተወሰነ ግዜ የህዝባዊ ሃይሉ አባል እንደነበረ ገልጸውልን፣ ስለግለሰቡ ያጠናቀርናቸው መረጃዎች ትክክል መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ሆኖም ግን ይህ ግለሰብ በወያኔ ደህንነት ቢሮ አማካይነት ተዘጋጅቶ እንዲበተን ባደረገው ሰነድ ውስጥ በሰፈሩ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ አስተያየት እዲሰጡን ጠይቀን የሰጡን ምላሽ፣
“ይህ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል መርህ ነው። የወያኔ ደህንነትና ፕሮፓጋንዲስቶችም ሆኑ ከህዝባዊ ሀይላችን ያፈነገጡና የከዱ ሰዎች ህዝባዊ ሀይላችንን በተመለከተ ለሚያሰራጯቸው የሀሰትና የፈጠራ ታሪኮች መልስ ስንሰጥ አንገኝም፣ ዛሬም ብቻ አይደለም ወደፊትም አቋማችን ይህ ነው የሚሆነው። በኛ እምነት ህዝባዊ ሀይላችን መግለጫ እና መረጃ የሚሰጠው የወያኔን እብሪት ለማስተንፈስ የተወሰዱ እርምጃዎችን ለህዝብ ለማብሰር እና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ነው። ቴዎድሮስ በሚል ስም በወያኔ ስለላ ድርጅት የተጻፈው ሰነድ ወያኔ ገና ከጥዋቱ ህዝባዊ ሀይሉ ምን ያህል እንዳሰጋው የሚያመላክት በፈጠራ ድርሰት የተሞላ ነው። ይህ ምላሽ የሚያስፈልገው አይደለም” ብለዋል። አያይዘውም “በእንደዚህ ያለ ቀውጢ እና ሰው የጠፋ ዕለት ሰው በሚያስፈልግበት ጊዜ በርካታ አንድ ለእናቱዎች የሚፈጠሩትን ያህል በርካታ ባንዳዎችም እንደሚፈጠሩ ታሪክ ብዙ ይነግረናል:: ይህ ግለሰብ በደቡብ አፍሪቃ በነበረበት ወቅት ያሳይ የነበረው ጸረ ወያኔ አቋምና አሁን በወያኔ ጉያ ተሸጉጦ የሚሰራውን የወያኔ ተላላኪነት ስራ ለተመለከተ በዚህ የትግል ወቅት የፖለቲካ ድርጅቶች ከወያኔ ሰዎች ቡርቦራ ራሳቸውን ለመከላከል ብዙ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ትልቅ ትምህርት የሚያስተምር ነው” ብለዋል።

No comments:

Post a Comment