የወያኔ ኢ.ሓ.ድ.ግ. መንግሥት በተለያዩ ክልሎች፣ በተለይም በቤኒሻንጉል-ጉሙዝና በጉራፈረዳ፣ በአማራ ተወላጆች ላይ
የከፈተው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ያሳዘናቸውና ያስቆጣቸው በምእራብ አውስትራሊያ የፐርዝ ከተማ ኗሪዎች ሰሞኑን በመሰባሰብ ለጥቃቱ
ምላሽ ሰጥተዋል። ጥቃቱ በጥልቅ የተሰማቸው እነዚሁ የፐርዝ ኗርዎች በመጀመሪያ ኤፕሪል 14 ቀን 2013 ተገናኝተው ምን
እናድርግ? በማለት በሰፊው የተመካከሩ ሲሆን፣ እንደገናም ኤፕሪል 21 ቀን 2013 ለሁለተኛ ጊዜ በመሰባሰብ አምስት አባላት
ያሉት አስተባባሪ ኮሚቴ በመምረጥና ወደ ተግባራዊ እንቅዝቃሴ በመሸጋገር ገንዘብ ማሰባሰብ ጀምረዋል።
አስተባባሪ ኮሚቴው መቋቋሙን ተከትሎ እንቅስቃቅሴው ስፋትና ጥለቀት ያገኘ ሲሆን፣ በተለይ ኤፕሪል 28 ቀን 2013 በተካሄደው ስብሰባ እርዳታው ለጥቃቱ ሰለባዎች በትክክል የሚደርሰበት ያአፈጻጸም ስልትና አብዛኛው የፐርዝ ኗሪ ኢትዮጵያዊ በእንቅስቃቅሴው በቀጣይነት ሊሳተፍ የሚችልበት እድል በሰፊው ተመክሮበታል። በስብሰባው ላይ ታዋቂውን ሃገር ወዳድ አቶ ገብረመድህን አርአያን ጨምሮ በተለያዩ ሙያዎች ለሃገርና ለወገን አስተዋጾ የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን ተካፋይ ሆነዋል።
በዚሁ መሰረት እስከ አሁን ለተፈቃነሉት ወገኖቻችን መርጃ $10,200.00 (አስር ሺህ ሁለት መቶ ዶላር) የተዋጣ መሆኑን አስተባባሪ ኮሚቴው አስታውቋል። እርዳታው ገና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም በተጨማሪ ገልጿል።
እሁድ ኤፕሪል 28 ቀን 2013 ከቀኑ 2፡00 እስከ 6፡00ፒ.ኤም. በሎፍተስ የመዝናኛ አዳራሽ በተካሄድው በዚሁ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከተለያየ አቅጣጫ በሰፊው የተገመገመ ሲሆን የሚከተሉት ነጥቦች በጉልህ ታሳቢ ሆነው ነበር፤
1. የስርዓቱ መሪ የሆነው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ሥልጣን ለመጨበጥም ሆነ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የቀየሰው ቀዳሚ እስትራቴጂ የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘርና በሃይምኖት መከፋፈል መሆኑ ተወስቶ በዚህ አኳያ በተለይ አማራውን በጠላትነት በመፈረጅ የማያቋርጥ ጥቃት እንዲፈጸምበት መደረጉና የአሁኑ የአማሮች መፈናቀልም የዚያው ዓላማ ቀጣይ ተግባር መሆኑ ተሰምሮበታል፤
2. አሁን በመካሄድ ላይ ያለው አማሮችን የማፈናቀል ዘመቻ በህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች አዝማችነት የሚካሄድ ዘር-የማጥፋትና ጸረ-የሰው ዘር ወንጀል በመሆኑ፣ ወንጀለኞቹን ለመፋረድ የሚቻልበት ዘዴ ተመክሮበታል፤
3. ዛሬ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ፣ በተለይም፣ በአማሮች፣ በጋንቤላዎች፣ በአፋሮችና በሌሎችም ላይ የሚደርሰው የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የዘረኝነት፣ የሃብት ዘረፍና የማፈናቀል ተግባር፣ የኑሮ ውድቀትና ስደት በአጠቃላይ በሕዝቡ ላይ የተጣሉት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች የወያኔ ስርዓት ከስሩ ሲገረሰስ ብቻ የሚወገዱ በመሆኑ ሁሉም ወገን ስርዓቱን ለማንኮታኮት በጋራ እንዲነሳ ጥሪ ተደርጓል፤
4. ተስፋ ሰጪ ከሆኑት የቅርብ ጊዜ ክስተቶች መካከል ደግሞ በነባሮቹ የኦሮም ነጻነት ግንባር መሪዎች አዲስ የተቋቋመው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦ.ዲ.ግ.) ወደ መድረኩ መምጣትና የኢሳት መጠናከር መበረታታትና መደገፍ ያለባቸው እድገቶች መሆናቸው ተወስቷል።
በመጨረሻም ከሁሉም ነገር በላይ አሁን ተፈናቅለው በስቃይ ላይ ለሚገኙት ወገኖቻችን የድረሱልን ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አጣዳፊ ተግባር በመሆኑ ገንዘብ የማዋጣቱ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጽኑ ማሳሰቢያ ተሰጥቶ ስብሰብው ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘለዓለም ትኑር!!
አስተባባሪ ኮሚቴው

No comments:
Post a Comment