March 19, 2013
ፕሮፌሰር ዩኪአም ሄርዚግ ከዚህ ቀደም በሁለት የዩኒቨርስቲዉ ምክትል ፕሬዚዳንቶች አሿሿም ላይ ዩኒቨርሲቲውን በበላይነት ከሚመራው ቦርድ ጋር አለመግባባት መፍጠራቸው የሚታወቅ ሲሆን ሁለቱን ተሿሚዎች በተመለከተ ለቦርዱ የጻፉትን ደብዳቤ በአስቸኳይ እንዲቀለብሱ ማስገደዱ ይታወቃል። አንድ ስማቸዉ እንዳይገለጽ የጠየቁ የዩኒቭርሲቲዉ ከፍተኛ ባለስልጣን ቦርዱ ፕሮፌሰር ሄርዚግ ለምክትል ፕሬዚዳንትነት ያጩዋቸውን ግለሰቦች ሳይቀበልና በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ሳይሰጥበት ለሦስት ወራት ያህል ቆይቶ አሁን ግን ሃያ አራት ሰአት በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ለመሾም መቿኮሉ የሚገርመና ግራ የሚያጋባ ነዉ ብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ቴድሮስ ሓጎስ ለዩኒቨርስቲዉ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ሄርዚግ ከኃላፊነታቸው የተነሱት የትራንስፎርሜሽኑን ዕቅድ በሚገባ በስራ አልተገበሩም በሚል እንደሆነ ሲሆን ከእሳቸዉ ሌላ የዩኒቨርሲቲው ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ምክትል ፕሬዚዳንት ወልፍ ቫን ፊርክስንና በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶክተር ዩአኪም ሌንገርትን ቦርዱ ከኃላፊነታቸው ማንሳቱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ሁለቱም ጀርመናውያን ከኃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያትም የአቅም ማነስና የአፈጻጸም ችግር የሚል መሆኑንም የዩኒቨርሲቲው መምህራን ገልጸዋል፡፡
No comments:
Post a Comment