በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁናቴ ህዝቡ ዕድሉን አግኝቶ ወደውጭ የወጣ እንደሆነ ወደ ዓገር ቤት ተመልሶ ቢገባ የጭንቅላት በሽተኛ ወይም እንደ እብድ አልያም እንደ ሞተ
ሰው ተቆጥሮ የህድር ጡሩንባ ተለፍፎ ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ የሚላቀስበት አልያም ደግሞ ከቤተሰብ ትዳር አንስቶ የሰፈር ሰው ትንሽ ትልቁ የስራ ባልደረባ ከታክሲ ሹፌር እስከ ዶክተር እስከ ትልቁ የወያኔ አገዛዝ ሚኒስቴር ድረስ እንደዘመኑ በሽታ ታይቶ የምትገለልበት ወሬው ሁሉ እንትና ደቡብ አፍሪካ ጠፋ በሞያሌ በሱዳን ሊቢያ እየተባለ ስንቱ ተስፋ ቆርጦ የሱሰኛ ተገዢ የሚደረግበትዘመን። ሌላው ይቅርና እትብቱ ወደተቀበረበት ሃገር ለመመለስ እንኳን የወያኔ ገዢ ፓርቲ 10 ግዜ እንድናስብ የሚነግረን ወቅት እንደነገሩ ተበልቶ አንዲት ለስላሳ ለመጠጣት 20 ግዜ የሚታሰብበት ቢራ ለመጠጣት ዱቤ ለመጠየቅ 40 ግዜ የሚታሰብበት ሃገር። ስለ እውነት ስለነጻነት ቢጠየቅ ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚችል መልሱን ? ..ለነሱ………የሚባለበት ግዜ ።
መቼስ አገሩ ላይ መኖር የሚጠላ ስው ያለ አይመስለኝም ግና ገና አካሉ አገሩ ላይ ቍጭ ብሎ መንፈሱ ውጭ አገር ያለውን ስንቱ ይቍጠረው። በውጭ ሃገር የሚኖረውማ ወደ ሃገሩ ተመልሶ ሃገሩ ላይ ሃገሩን ወገኑን ለማገልገል የፈለገ ሰው ሃገሪቷ ላይ መኖር የማይችልበትን የጥቂት ዘረኛ ወያኔ አገዛዝ መንግስት የሚኖርባት በመሆኑ ለማድረግ አይችልም። በዛ ላይ ሰሞኑን ያየሁት የሰለሞን ቦጋለ እና ሳምሶን ቤቢ ፊልም በጣም ሲከነክነኝ ነው የዋለው አዎ የዚህ ደራሲ በፈለገው መልኩ ይጻፈው እኔ በተረዳውት ግን ለዚያች አገር ለዛ ህብረተሰብ ነጻነት ያስፈልገዋል ። መልዕክቱን በፈለጉት መልኩ ያስተላልፉት ግን በደንብ የሚታይ ነገር ነበረበት ስለነጻነት ብሩህ ተስፋ ።
ለነገሩ ወያኔዎች አገራቸው አይደልም የመጡበትን ዓላማ አሳክተዋል። የስራውን ይስጠውና ሟቹ ስሙን ቄስ ይጥራውና አገሪቷን በዘር በዓይማኖት በብሄር ከፋፍሎ ሰዉ በጎሪጥ እንዲተያይ አድርጎት እሱ ወደማይቀረው ሄዷል ምን አለ የሱ ተከታዮችም ይሄ መኖሩን አውቀው ወደ ህዝቡ በተመለሱ። አገሪቷማ ስንቱን አሳድጋ እንጡራ አብቷን አውጥታ ያስተማረችውን የተማረ ዓይል ስንት ድግሪ ፕሮፌሰር ያደረገችውን ሃገር እየተወ መመለሻም መቀበሪያም ላትሆነው ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተሰድዶ በአሁኑ ሰዓት በስደት ላይ ይኖራል ። እንዲህም ሆኖ ለሃገር የተቆረቆሩ የሚመስሉ ከሃዲ ሆዳም እነዚህን ሰዎች ባሉበት ቦታ እንኳን እንዲቀመጡ አያደርጓቸውም እንዲያውም ብለው ወያኔ ለሃገር እንደሚቆረቆር ያወራሉ ለነገሩ የትኛው የወያኔ ሃገዛዝ መንግስት ነው ለሃገሩ የሚቆረቆረው በዛ በበረሃ የማንም ተኩስ መለማመጃ ሆነው እነደሻማ ቀልጠው ሲቀሩ ሴት እህቶቻችን ማንም ሳይደርስላቸው እንደበግ መሬት ለመሬት ሲጎተቱ ዝም ብሎ በደፈናው ሃገር ሃገር ማለት መብራትና ውሃ በሌለበት ሰዉ በፈለገውና በሚታየው መልኩ የራሱን ሃሳብ መግለጽ የማይችልበት ከታክሲ ዳቦና ወዘተ የመሳሰሉት ሰልፍ በስተቀር 3 ሰው እንኳን አብሮ ቆሞ ማውራት የማይቻልበት ወያኔ ለህዝቡ ካልሰረቀና ሙስና ካልሰራ መሻሻል የማይቻልበት ሃገር ለዚች አገር ነው ተቆረቆረ የሚባለው። ውድ ወገኖች ስለዚህ ለዘመናት ባአባቶቻችን በጥረታቸው የተገነባች የገነቧትን ሃገር ወያኔ ደግሞ በግዴለሽነት በዘረኝነት እየፈራረሳት ይገኛል ። ህዝቡንም በትልቅ የሞራል እስር ቤት ውስጥ አስረውት ይገኛል ከዚህ እስር ቤት የሚያወጣው አንዳች አይል ያስፈልገዋል ። የኢትዮጵያን ህዝብ ክብር በማንኛውም መንገድ ማስመለስ ይኖርብናል ህዝቡ በእየለቱ በሚሰማው ነገር ልቡ ሸፍቷል ከጥቂት ሆዳሞች በስተቀር ስለዚህ ይኼ የነገዋ ኢትዮዽያ ቀን ነዉ የኔ የእናንተ ብ ቻ ሳይሆን የመላዉ ኢትዮዽያ ጥያቄ ነዉ እንድረስላት ይህን ሳናደርግ የቀረን እንደሆነ ግን ህሊና ቢስ ነን ፍሬ ቢስ ነን ወይም ደግሞ ከሃዲ ነን
እግዚሃብሄር ኢትዮጵያንና ተከባብሮ የሚኖረውን በማንኛውም ዓይማኖት ላይያለውን ህዝብ ይባርክ
አሜን
ያሬድ ኤልያስ
No comments:
Post a Comment