March 14, 2013
ኢትዮጵያዊያንን አፍኖና ረግጦ አንድ ለአምስት በተሰኘ አደረጃጀት እስከቤተሰብ የወረደ የስለላ ተግባርን እየፈጸመ ያለው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ የግንቦት 7 ንቅናቄን መረጃ ለማግኘት ከፍተኛ የሆነ የስለላ ተግባር ሲፈጽም እንደቆየ ተቀማጭነቱ አውሮፓ የሆነ አንድ አለማቀፍ የሶፍት ዌር ኩባንያ አጋለጠ።የወምበዴዎች ጥርቅም የሆነው የወያኔ አገዛዝ በስሩ ለዚሁ ተግባር ያቋቋመው ኢትዮ ቴሌኮም ፊን ሰፓይ በመባል የሚታወቀውን ሶፍትዌር በመጠቀም የግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ መረጃዎችን ሲሰልል መገኘቱን ያጋለጡት ሞርጋን ማርኩዊስ ቦሪ፣ ቢል ማርዛክ ፣ ክላውዲዮ ጋርኔሪ እና ጆን ስኮት በመባል የሚታወቁ ባለሙያዎች ሬይላተን ሲትዝን ላብ በተባለ ዌብሳይት ላይ ባወጡት ጽሑፍ ነው።
እነኝሁ ባለሙያዎች ፊን ስፓይ የግንቦት 7ትን መሪዎች ፎቶግራፍ ወደ ኮምፒዩተር ተጠቃሚዎች በመላክ መረጃዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ለማቀበል መሞከሩን የገለጹ ሲሆን የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ኢንተለጀንስ በበኩሉ ፣ የወያኔው አፋኝ አገዛዝ ከድርጅቱ መረጃዎችን ለመውሰድ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ እንደነበር መረጃዎች እንዳሉት አስታውቋል።
የድርጂቱ መረጃዎች ወደ አፋኙ አገዛዝ እጅ አለመግባታቸውን ያረጋገጠው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ድርጅቱ በስልጣን ላይ ካለው ዘረኛና አፋኝ የወያኔ አገዛዝ ጋር ከፍተኛ የሳይበር ጦርነት ሲያድረግ እንደነበር ም ታውቋል።
ፊን ስፓይ ወንጀለኞችን ለመያዝ ተብሎ የፍትህና የደህንነት ሰራተኞች እንዲጠቀሙበት በሚል መነሻ የተመረተ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ እንደወያኔ አገዛዝ ያሉ አፋኝ መንግስታት ሶፍትዌሩን ተቃዋሚዎቻቸውን በስፋት ይጠቀሙበታል።
No comments:
Post a Comment