Tuesday, November 12, 2013

ወያኔ ማለት ቁምጣ ለብሶ የመጣ ደርግ ነው ፡፡

http://www.facebook.com/photo.php?v=286230021510610
ጥቁር ሽብር ወያኔ ቁምጣ የለበሰ ደርግ ነው ! እመኑኝ በየትኛውም የታሪክ ገጠመኝ የሳወዲ መንግስት የዚህ አይነት ድፍረት ያውም በአደባባይ በዜጎቻችን ላይ አሳይቶ አያውቅም ፡፡ ነገሮችን ተመልሰን ከተመለከትን ይህ ግፍና በደል የእኛው ባለስልጣናት ሳውዲወችን አደፋፍረው ያስፈፀሙት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ሁለት ፖለቲካዊ ምክንያቶች አሉት ፡፡ የመጀመሪያው ፡- የወያኔ ባለስልጣናት በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያንን ቦንድ እንዲገዙ በሰበሰቡበት ወቅት ተደጋጋሚ ተቃውሞ ደርሶባቸው እንደነበር የሚታወቅ ነው ፡፡ ይህም ድምፃችን ይሰማ ባሉ ሙስሊሞች ላይ በሃገር ውስጥ የሚደርሰው በደል ይቁም ለጥያቂያቸውም አጥጋቢ መልስ ይሰጥ በሚል ምክንያት ነበር ፡፡ ቂመኛው መንግስታችን ይህን እንደበደል በመቁጠር በእጅ አዙር ዜጎቻችንን እያስጋዘ ይገኛል ፡፡ ለዚህ በደሉ ሽፋን እንዲሆነው በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያወቹ አረብ አገራት ላይ ያተኮሩ ወሬወችን ሲነዛ ቆይቷል ፡፡ የሳዲ መንግስት በሰጠው የጊዤ ገደብ የሚያስፈልጋቸውን መረጃ ሊጠይቁ ወደ ‹‹ኢትዮጲያ ኤምባሲ ›› የሄዱ ሚስኪን ለፍቶ አደሮች ቦንድ ግዙ እየተባሉ ሲመላለሱ የጊዜ ገደቡ አልቆላቸዋል ፡፡ ሁለተኛው ምክንያቱ ፡- አገር ውስጥ ያለው ‹‹የድምፃችን ይሰማ ›› እንቅስቃሴ አረብ አገራት ባሉ ኢትዮጲያዊያን የገንዘብ ድጋፍ ያገኛል በሚል ፍርሃት ነው ፡፡ፍርሃት ብቻ ሳይሆን በግልፅም በወቲቪ (የ ወያኔ ቴሌቪዥን ) በተደጋጋሚ ተናግሮታል ፡፡ በመሆኑም ይህን የራሱን ስጋት ለማስታገስና መመለስ ያልቻለውን የማይችለውንም የመብት ጥያቄ ለማፈን የገቢ ምንጭ ናቸው ያላቸውን በአረብ አገር የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያንን ሰላም ደህንነትና ሂወት ጭምር በእጅ አዙር እየነጠቀ ነው ፡፡ (እዚህ ላይ ሳውዲወች የቴውድሮስ አድሃኖም ስምምነት አለበት ማለታቸውን እንዳንዘነጋ) አሁን ከወደኪዌት እንደምንሰማው ደግሞ ከስራቸው በገፍ የተፈናቀሉ ኢትዮጲያዊያን ሰልፍ እንወጣለን አልያም ስራ ይሰጠን እያሉ ነው ፡፡ እኒህ ኢትዮጲያዊያን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከስራቸው የተፈናቀሉ ናቸው ፡፡
ወያኔ እና የወያኔ ጭፍን ደጋፊወች ማወቅ ያለባችሁ ጉዳይ ድህነት ትግልን ያባብሳል እንጅ አያዳፍንም ‹‹አፈር እየቃምን ድንጋይ እየቆረጠምን ደርግን ጣልነው ›› እንደምትሉት ይህም ህዝብ ሆነ ብላችሁ የምትጭኑበትን ድህነትና እንግልት ተቋቁሞ ድል ማድረጉ የማይቀር ነው ፡፡ ታውቁታላችሁ እናውቀዋለን ! ወያኔ ማለት ቁምጣ ለብሶ የመጣ ደርግ ነው ፡፡ ደርግ ቀይ ሽብር ብሎ ህዝብ ፈጀ ፤ ወያኔ በተዳፈነና የህዝብን መብት ፣ ነፃነትና ሂወት ጭምር በጋረደ ጨለማ አገዛዙ ጥቁር ሽብሩን አወጀ፡፡ እነሆ አገራችን በጥቁር ሽብር ውስጥ ወድቃለች ንጋትን ናፍቆ የተሰደደ ህዝብ በገፍ እየተሰቃየ ነው ፡፡
Sekota Wollo Ethiopia

ብሄራዊ ውርደት፤ የምንመጻደቅበት ‘ሌጋሲ’ (ክንፉ አሰፋ)

    
ወገናችንን በጥይት ሲደፉት በራሱ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንድራችንን ጠምጥመውበታል[1]። ጭካኔ በተሞለበት መንገድ የተገደለው ይህ ኢትዮጵያዊ አስከሬኑም በሰላም አላረፈም። በአካሉ ላይ ያረፈውን ጨርቅ በሴንጢ እየቆራረጡ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ሊደረግ የማይገባውን ሁሉ አደረጉበት። ድርጊቱ ናዚዎች በኦሽዌትስ ይፈጽሙት የነበረውን አሰቃቂ ግፍ ያስታውሰናል። በ21ኛው ዘመን እንዲህ አይነቱ ክስተት ይደገማል ብሎ የሚያስብ የለም። እነሆ ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመችው ነው። በስውር ሳይሆን በግልጽ። እንደ ኦሽዊትስ በታጠረ የማጎርያ ካምፕ ሳይሆን በአደባባይ።
behageru-besawdi
ሰው ከሞተ በኋላ ለምን ሙት አካሉን ማሰቃየት አስፈለገ? ምን አይነት ጭካኔ ነው? ምን አይነትስ ጥላቻ ነው? ለሳውዲዎች ግማሽ ፈረንሳይን የሚያህል መሬት ሰጥተናቸው የለም እንዴ? ሀጥያታችን ምኑ ላይ ነው ታዲያ? አስከሬኑን ውሻ፣ ውሻ ሲሉ ሲሳለቁበት ከማየት በላይ የሚያም ነገር የለም። በአደባባይ እንደዋዛ የተጣለው አስከሬን በእርግጥ የዉሻ አስከሬን ቢሆን ኖሮ የእንስሳ ተከራካሪዎች አለምን ቀውጢ ባደረጓት ነበር። Read full story in PDF…
EMF