Sunday, May 19, 2013

ግንቦት 7 የፖለቲካ ድርጅት እንዳልሆነ ያውቁ ኖሯል?

 

አሰፋ ከዳላስ
ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 3፣ 2005 (May 11, 2013) በዳላስ ከተማ በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌ ቪዥን (ኢሳት) የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነበር:: እጅግ በጣም የተሳካ እና የደመቀ ፕሮግራም ነበር:: ታዲያ በዝግጅቱ ላይ ትኩረቴን የሳቡት ብዙ ነገሮች ቢኖሩም በዚች አጭር ፅሁፌ የማተኩረው የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ያነቧት ዘንድ ተሰራጭታ በነበረችው እና እኔም እጅ በገባችው አንዲት በራሪ ወረቀት ላይ ነው::Ginbot 7 press release in Amharic
ይቺ አንድ ገፅ በራሪ ፅሁፍ ስለ ግንቦት 7 ድርጅት የምታወራ ሲሆን ርዕሷም ግንቦት 7ን ያውቁት ኖሯል? የሚል ነው:: በበራሪ ወረቀቷ ላይ እንደተጠቀሰው “ግንቦት 7 ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች የሚለይበትን ዋና ነጥብ ተረድተዋል?” ይልና እንደ ምክንያትም “ግንቦት 7 የትምህርት: የኢ ኮኖሚ: የውጪ ጉዳይ… ወዘተ ፖሊሲ የለውም” በማለት ያትታል:: ርግጥ ነው አንድን ድርጅት የፖለቲካ ድርጅት ከሚያሰኙት ነገሮች ውስጥ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች እንደሚገኙበት አያጠራጥርም::
ከላይ በጠቀስኳት በራሪ ፅሁፍ ላይ የተገለፁት ነጥቦች እንደተጠበቁ ሆነው በእኔ ግምት ግንቦት 7ን ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች የሚለየው ዋናው ምክንያት የፖለቲካ ድርጅት ባለመሆኑ ይመስለኛል:: ይህን ስል ግንቦት 7 ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ድርጅት አይደለም ለማለት እንደማይዳዳኝ አንባቢ እንደሚገነዘብልኝ እርግጠኛ ነኝ:: በአንድ ሀገር ውስጥ ፍትህና: ዲሞክራሲ እንዲሰፍን: የህግ የበላይነትና የመንግስት ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የሚታገልን ድርጅት ፖለቲካዊ ይዘት ወይንም ፖለቲካዊ አላማ የለውም የሚል ሰው ካለ የሚናገረውን ነገር የማያውቅ ብቻ ነው:: እኔ ግንቦት 7 የፖለቲካ ድርጅት አይደለም ስል የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም ማለቴ ነው::
ለመሆኑ የፖለቲካ ፓርቲ ማለት ምን ማለት ነው? የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ይቅርታ እንደሚያደርጉልኝ ተስፋ አደርጋለሁ:: ከተሳሳትኩም ለመታረም ዝግጁ ነኝ:: እኔ እንደገባኝ የፖለቲካ ፓርቲ ማለት በአንድ ሀገር ውስጥ ወይንም በአንድ ፖለቲካዊ ማህብረሰብ ውስጥ በየደረጃው ያለ የመንግስት ስልጣንን ለመያዝ የሚጥር ይህንን ለማሳካትም የራሱን ፕሮግራምና ስትራቴጂ ቀይሶ የሚንቀሳቀስ የሰዎች ስብስብ (ድርጅት) ነው:: ይህ ከሆነ አንድ የፖለቲካ ድርጅት የመንግስት ስልጣን ለመጨበጥ ከሌሎች ተመሳሳይ አላማ ካላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር መወዳደር አለበት:: ፕሮግራሙን ለህዝብ ማሳወቅ አለበት:: ህዝብን ማሳመን አለበት (በጠመንጃ ወይንም በሀይል የመንግስት ስልጣን ስለሚያዝበት ህብረተሰብ ካላወራን በስተቀር ማለቴ ነው)::
በእኔ የፖለቲካ ፓርቲ ምንነት (Definition) ላይ ከተስማማን የፖለቲካ ፓርቲ በአንድ ሀገር ውስጥ አለ ለማለት 3 ነገሮች መሟላት አለባቸው::
1. የዚያ ድርጅት ዋና አላማ (ግብ) የመንግስት ስልጣን መያዝ ከሆነ
2. ድርጅቱ መወዳደርና ፕሮግራሙን ለህዝብ ማሳወቅ የሚችልበት የተመቻቸ ሁኔታ ካለ
3. ድርጅቱ መወዳደር ብቻ ሳይሆን ተወዳድሮ ካሸነፈ የመንግስት ስልጣንን የሚረከብበት የተመቻቸ ሁኔታ ካለ
የመጀመሪያውን ቅድመ ሁኔታ በተመለከተ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የወቅቱ የኢትዮጵያ ችግር ያገባናል በማለት የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በተለይ በውጪ የሚገኙት አንዳቸውም ዋና አላማችን (ግባችን) የመንግስት ስልጣን ለመያዝ ነው ሲሉ አይደመጡም:: 2ኛ እና 3ኛ ላይ የተቀመጡት ሁኔታዎች ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሌሉ ግልፅ ነው:: እንግዲህ በኔ ስሌት ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ፓርቲ የለም ወይንም ሊኖር አይችልም ማለት ነው::
ብዙ ግዜ ከማውቃቸው ሰዎች ጋር ስለ ግንቦት 7 አንስተን ስንጫወት ግንቦት 7 የፖለቲካ ድርጅት (ፓርቲ) አይደለም ስላቸው ብዙዎቹ ግራ ይገባቸዋል:: ይህንን የምልበት አንዱና ዋናው ምክንያት እራሱ ግቦት 7 ያስቀመጠውን ፕሮግራም በማየት ነው:: ከላይ እንደገለፅኩት ከወቅቱ የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ሲታይ የፖለቲካ ፓርቲ የለም ወይንም ሊኖር አይገባም ብዬ ስለማምንም ነው:: ግንቦት 7 በፕሮግራሙ ኢትዮጵያ ውስጥ መወዳደርም ሆነ ሀሳብን ማራመድ ተወዳድሮም በሀሳብ ማሸነፍ የማይቻል መሆኑን: በሀገሪቱ ላይ የሃይል አገዛዝ የሰፈነ መሆኑን በማያሻማ መልኩ ያስረዳል:: የግንቦት 7ን ፕሮግራም ላነበበ ሁሉ የድርጅቱ ዋና አላማ (ግብ) የመንግስት ስልጣን መያዝ ሳይሆን የመንግስት ስልጣን በምርጫ ብቻ የሚያዝበትን ሁኔታ በሀገሪቱ እንዲመቻች መታገል መሆኑን በግልፅ ይረዳል::
የሁሉንም ድርጅቶች ፕሮግራም ጠንቅቄ ባላውቅም የግንቦት 7ን ያህል ኢትዮጵያ የገባችበትን አጣብቂኝና የተጋረጠባትን ፈተና በአግባቡ የተረዳ ያንንም በፕሮግራሙ ላይ ቁልጭ አድርጎ ያስቀመጠ መኖሩን እጠራጠራለሁ:: ይህም ግልፅነት የመነጨው በኔ ግምት ነነፃነት እና ፍትህ በአንድ ሀገር ላይ እንዲሰፍን መታገል: የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ ስልጣን ላይ ለመውጣት ከሚደረግ ትግል ጋር የተለየ መሆኑን በሰከነ መንፈስ ከመረዳት ይመስለኛል፡፡ ርግጥ ነው የአላማ ጥራት ብቻውን የሚፈለገው ውጤት ላይ ለመድረስ በቂ አይደለም:: ያንን ያስቀመጡትን አላማ ከግብ ለማድረስ ብዙ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል:: ነገር ግን ችግሩን በአግባቡ ተረድቶ ለችግሩ መፍቻ የሚሆን እቅድና አላማ በግlልፅ ማስቀመጥ ሊታለፍ የማይገባው የመጀመሪያ ርምጃ ነው:: እንደ እኔ ከሆነ ግንቦት 7 ይህንን የመጀመሪያ ርምጃ በተሳካ መልኩ ተራምዷል::
እኔን ግራ የሚያጋቡኝ እራሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲ እያሉ የሚጠሩት ናቸው:: የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ድረገፅ ስንመለከት በምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ 79 ‘የፖለቲካ ፓርቲዎች’ ይገኛሉ:: ይህ እንግዲህ በሀገር ውስጥ ያሉትን ብቻ እንጂ ከሀገር ውጪ ራሳቸውን ‘የፖለቲካ ፓርቲ’ ብለው በመጥራት የሚንቀሳቀሱትን አይጨምርም:: ምክንያቱም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከሀገር ውጪ የሚገኙ ድርጅቶችን በፖለቲካ ፓርቲነት የሚመዘግብ አይመስለኝም:: መቼም ከነዚህ መካከል በልጣን ላይ ያለው ቡድን ለስም ያስቀመጣቸው ለኖሩ እንደሚችሉ መገመት ከባድ አይደለም:: ሌሎቹስ በራሳችን ተቋቁመናል የሚሉት ርግጥ በሀገራችን ተጩባጭ ሁኔታ በፖለቲካ ፓርቲነት መንቀሳቀስ ውጤት አለው ብለው አምነውበት ነው?
የመወዳደሪያ ሜዳ በሌለበት በሌለበት: የመሮጫው ህግ ባልተወሰነበት: ያለውም ህግ በማይከበርበት ሁኔታ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ በጋራ መስራት ነው ወይንስ እየተነሱ መሮጥ ነው የሚቀድመው? በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እራሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲ እያሉ የሚጡሩት እነዚህን ነገሮች ያሰቡባቸው አይመስለኝም:: በበኩሌ ከፈረሱ ጋሪው ቀድሟልና ይታሰብበት::
በነገራችን ላይ የግንቦት 7 አድናቂ እንጂ አባል አይደለሁም::

May 18, Tribute to Mr. Abebe Gelaw

Mr. Abebe Gelaw, Journalist and Human Rights Activist

by Robele Ababya
This day marks the 1st Anniversary of that unforgettable occasion on 18 May 2012 that your call for freedom at the Regan Memorial Building in Washington, at the meeting of world leaders and dignitaries chaired by President Obama. The man that you quite rightly labeled “Meles Zenawi is a dictator” was seen shaken, drooping, scared and demoralized in that Hall. He shamed his cohorts that are engaged in building his personality cult crowning him with the accolade: “Statesman leading Africa and a fearless commander of a fighting guerrilla force that shook the mountains”. To hide their utter embarrassment they even profusely disseminated the tyrant’s photograph sitting on a tank reading a book.
18 May 2012 Abebe Gellaw's call for freedom
18 May 2012 Abebe Gellaw’s call for freedom at the Regan Memorial Building in Washington.
Your clear call reverberated in our global village of the age of information and promptly elevated the moral of Ethiopians; it instilled renewed hope and resolve to unite the forces of change in their struggle against the dictatorial TPLF/EPRDF regime well-armed to the teeth and supported by the Western powers.
In my opinion, unity of the Ethiopian people, opposition political forces, and independent civil societies is now on a steady march to eradicate tyrannical governance once and for all. The scattered anger has been gathering in the course of the year (since 18 May 2012) to the point of becoming a formidable force, which is able to deal with the atrocious legacy of Meles Zenawi who was publicly calling well-meaning opposition entities his enemies.
Your creative choice of venue, timing, and the words of message will no doubt admirably go down in the annals of the history of a liberated Ethiopia.
Sincerely,
Robele Ababya
rababya@gmail.com